ኮቪድ-19- የጠያቂዎች መመሪያ

(ሰኔ 11 ቀን 2012 ዓ.ም)

የእኛ የታካሚ እንክብካቤ ፍልስፍና የቤተሰቦች እና ጓደኞች ተሳትፎ ለመዳን ሂደት በርካታ ጥቅሞች እንዳሉት ዕውቅና ይሰጠዋል።  ይሁን እንጂ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ  ከመጣ ጀምሮ ተጨማሪ እርምጃዎች በመውሰድ የእኛን ታካሚዎች፣ ጠያቂዎችን እና ሠራተኞች እንዲሁም የተለመደውን የታካሚ ጥየቃን ማጥበብን ጨምሮ በዋሽንግተን ዩኒቨርስቲ ሐኪም ቤቶች፦ በሀርበርቪው ሕክምና ማዕከል፣ በዋሽንግተን በዩኒቨርስቲ ሕክምና ማዕከል-ማውንት ሌክ፣ በዋሽንግተን በዩኒቨርስቲ ሕክምና ማዕከል-ኖርዝዌስት እና ቫሊ የሕክምና ማዕከል( Harborview Medical Center, UW Medical Center – Montlake, UW Medical Center – Northwest and Valley Medical Center)

በአሁኑ ጊዜ ሕመምተኞች ከዚህ በታች በተገለጹት ገደቦች እና የሚጠበቁትን መሠረት በማድረግ በሆስፒታሉ ውስጥ አንድ ጠያቂ ሊኖራቸው ይችላል።

ጠያቂዎች የመተንፈሻ አካል በሽታ ሕመም ስሜት ምልክቶች ካላቸው ለማወቅ የተመደቡ የመግቢያ በሮች ላይ ምርመራ ይደረግላቸዋል። እነዚህ ምልክቶች ሳል፣ የትንፋሽ እጥረት ወይም ለመተንፈስ መቸገር፣ ትኩሳት፣ ብርድ ብርድ ማለት፣ የጡንቻ ህመም፣ የጉሮሮ መቁሰል፣አዲስየጣዕም ወይም የሽታ ስሜት ማጣት፣ ራስ ምታት፣ ንፍጥ እና የጨጓራ ሕመም ምልክቶች እንደ ማቅለሽለ፣ ማስታወክ ወይም ተቅማጥ ናቸው።  ማንኛውም ጠያቂ እነዚህ የሕመም ምልክቶች ካሉት ዋሽንግተን ዩኒቨርስቲ ሕክምና ማዕከል ለመግባት አይፈቀድለትም። እነዚህ ስሜቶች የሌለው ብቻ ነው ለመግባት የሚፈቀድለት። እንዲሁም የታካሚ ጥየቃ በእያንዳንዱ ሆስፒታል የጥየቃ ሰዓታት እና መመሪያዎች የተገደበ ነው።

 • እያንዳንዱ ጠያቂ በሆስፒታል ተቋም ውስጥ በማንኛውም ጊዜ ጭምብል መልበስ አለበት።
 • ጠያቂዎች ወደ ሐኪም ሲደርሱ ወይም ከሐኪም ቤቱ ለቀው ሊወጡ ሲሉ ካልሆነ በቀር ሕመምተኛው ክፍል ውስጥ መቀመጥ አለባቸው።
 • ዕድሜያቸው 16 ዓመት በታች ለሆኑ ሕመምተኛ መጠየቅ አይፈቀድም።
 • ዕድሜያቸው 18 በታች ለሆኑ ሕመምተኞች አንድ ጠያቂ፣ ወይም ወላጆች ወይም አሳዳጊዎች ሊኖራቸው ይችላል።
 • በማዋለጃ ክፍሎች ውስጥ ሕመምተኞች ሁለት ጤናማ የድጋፍ ሰጪ ግለሰቦች በምጥ ጊዜ ይፈቀድላቸዋል።  ከወለዱ ከሁለት ሰዓታት በኋላ አጠገባቸው እንዲቀር የሚፈቀደው አንድ ድጋፍ ሰጪ ብቻ ሲሆን ሁለተኛው ግለሰብ ሆስፒታሉን ለቆ መውጣት ይኖርበታል።
 • የሕይወት መጨረሻ ደረጃ ላይ ላሉ ሕመምተኞች ሁለት ጠያቂዎች ሊኖራቸው ይችላል፦
  • የሕይወት መጨረሻ ላይ ያሉ ታካሚዎች የሚባሉት በመጪዎች ጥቂት ቀናት ውስጥ የመሞት ዕድላቸው ከፍ ያሉ ሲሆኑ ግን የምቾት ሕክምና እርዳታ(የፓሊዬቲቭ ኬር)የሚያገኙትን አይገድብም።
  • እያንዳንዱ ክፍል ስራ አስኪያጅ  ክሊኒካዊ ጉዳዮች ላይ በመመርኮዝ የጥየቃውን ጊዜ ገደብ መወሰን መብት አለው፡፡
  • ለአካለ መጠን ያልደረሱ ጠያቂዎችች ከወላጅ ወይም ከአሳዳጊ ጋር ከሆኑ እና የእንክብካቤው ቡድን ከፈቀደ ብቻ መግባት ይችላሉ።  
 • በአእምሮ ወይም በእዕደገት ሁኔታቸው ወይም በአካል ጉዳታቸው ምክንያት የደህንነት ተንከባካቢ ለሚፈልጉ ታካሚዎች እንደ ዓይነ ስውር እና/ወይም የመስማት ችግር ካለ ከተንከባካቢዎቻቸው በተጨማሪ አንድ ጠያቂ ሊኖራቸው ይችላል።  
 • የቤት ተንከባካቢያቸው ሥልጠና የሚያስፈልጋቸው ታካሚዎች ከተንከባካቢው በተጨማሪ አንድ ጠያቂ ሊኖራቸው ይችላል
 • በታካሚው እንክብካቤ ውስጥ የሚሳተፉ ማህበረሰብ-ተኮር እንክብካቤ ሰጪዎች ከታካሚው አንድ ጠያቂ በተጨማሪ ለድጋፍ እና ለእንክብካቤ ቀጣይነት መጥተው ሊጢይቁት ይችላሉ ፡፡
 • ከአንዱ ጠያቂ በተጨማሪ ከመንፈሳዊ ማህበረሰብ አባላትታካሚውን መጠየቅ ይችላሉ።
 • ጠያቂዎች ዕቃዎች ወይም መሣሪያዎች ከሆስፒታሉ መውሰድ አይችሉም።
 • የዋሽንግተን ዩኒቨርስቲ ሕክምና ማዕከል ሠራተኞች ሐኪም ቤት የተኙ የቤተሰብ አባላት ካላቸው ይህ ጥብቅ የጠያቂዎች ገደብ እነሱንም ይመለከታል። 
 • ከሕይወት መጨረሻ ደረጃ ላይ ካሉ ሕመምተኞች በስተቀር (ከዚህ በላይ ይመልከቱ)ኮቪድ-19 አዎንታዊ ምርመራ ለተደረገላቸው ወይም በምርመራ ላይ ላሉ ሕመምተኞች ክፍል ውስጥ ለማንም ጠያቂዎች አይፈቀድም።
 • በአሁኑ ጊዜ በየትኛውም የሆስፒታል ተቋም ውስጥ ለሌሎች ጠያቂዎች መግባት አይፈቀድም። 

ለታካሚዎቻችን ለጠያቂዎቻችን እና ለሠራተኞቻችን የሚቻለውን የአካባቢ ደህንነት መስጠታችንን ስንቀጥል የእርስዎን ግንዛቤ መስጠት እናደንቃለን ፡፡ማንኛውም ዓይነት ጥያቄ ወይም አሳሳቢ ጉዳይ ካለዎት እባክዎን የጤና እንክብካቤ ቡድንዎን ያነጋግሩ።

አመሰግናለሁ

የማዋለጃ ክፍል ጠያቂዎች መመሪያ (በቀዶ ጥገና (ሲ-ሴክሽን) ወይም አምጠው ለሚወልዱ)

በዋሽንግተን ዩኒቨርስቲ ሕክምና (UW Medicine) የምጥ ጊዜ ወሳኝ ጊዜ ቢሆንም አስፈሪም ሊሆን እንደሚችል እንገነዘባለን በተለይም ኮቪድ-19 ጊዜ ፡፡ ወረርሽኙ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶእናትናሕፃኑን ደህንነት ለመጠበቅ  እርምጃዎችን ተግባራዊ አድርገናል፡፡  ባለን ፈጣንምርመራ ሒደት ለሠራተኞች ሁለንተናዊ ጭንብል እና ውስን የጠያቂዎች መመሪያ ማድረግ ደህንነቱ የተጠበቀና ጤናማ የሆነ የወሊድ ገዜ እንዲኖርዎ የተቻለንን ሁሉ እያደረግን ነው ፡፡

ከግንቦት 11  ቀን 2012 (May 19, 2020)ጀምሮ እናቶች-ለመሆን በዋሽንግተን ዩኒቨርስቲ ሕክምና- ማውንት ሌክ እና  በዋሽንግተን በዩኒቨርስቲ ሕክምና-ኖርዝዌስት ( UW Medicine – Montlake and UW Medicine – Northwest) ሐኪም ቤቶች በምጣቸው ጊዜ ጤናማ የሆኑ ሁለት ድጋፍ ሰጪዎች አብሯቸው እንዲሆኑ  ይፈቅድላቸዋል ፡፡

ይህ መመሪያ ለእርስዎ ለሕፃኑ እና ለመላው ማህበረሰብ ደህንነቱ የተጠበቀ አካባቢ በሚወልዱበት ጊዜ ድጋፍ እንዲኖርዎት ያደርጋል ፡፡ ለደህንነትዎ ሲባል የኮቮድ-19 ምልክቶች ወደ ሆስፒታል የሚመጡ ሰዎችን መመርመር እንቀጥላለን ፡፡ ምልክቶቹ ትኩሳት የሰውነት ህመም የጉሮሮ መቁሰል ሳል የትንፋሽ እጥረት እና ድንገተኛ ጣዕምና እና ማሽተት አቅም ማጣትን ሊያካትቱ ይችላሉ።

የወሊድ መመሪያችን የሚከተሉትን ጨምሮ ያካትታል ፡፡

 • ድጋፍ ሰጭዎችዎ ቢያንስ16 ዓመት ዕድሜ መሆን አለባቸው ፡፡
 • ከወለዱ ከሁለት ሰዓታት በኋላ አንድ ድጋፍ ሰጪ አጠገብዎ መቆየት ይችላል ነገር ግን ሁለተኛው ግለሰብ ሆስፒታሉን ለቆ መውጣት አለበት።
 • በምጥ ጊዜ በኮሪደሩ መተላለፊያዎች ውስጥ መራመድ አይችሉም ግን በክፍልዎ ውስጥ መንቀሳቀስ ይችላሉ ፡፡ ምግብ ወይም መጠጦች ከፈለጉ ሰራተኞቻችን እነዚህን ዕቃዎች በቀጥታ ወደ ክፍልዎ ያመጡልዎታል።
 • እርስዎ እና ድጋፍ ሰጪዎ አንድ ላይ በመሆን በወሊድ ጊዜ እና በአዲሱ ሕፃንዎ ላይ ለማተኮር እንዲችሉ እባክዎን የሌሎቹን ልጆችዎን ፣ የቤተሰብ አባላትን  እና የቤት እንስሳትን እንክብካቤ አስቀድመው ያዘጋጁ ፡፡
 • እባክዎን እዚህ በምትቆዩበት ጊዜ የሚፈያስልግዎትን ነገሮች በሙሉ የህፃን መኪና ወንበር እና የምትወዱትን ምግቦችን  ጨምሮ ይዘው  ይምጡ ፡፡

የእርስዎን ልጅዎን እናመላው ማህበረሰቡን ደህንነት ለመጠበቅተቻለንን ሁሉ በምናደርግበት ጊዜ ያለዎትን ግንዛቤ እናደንቃለን።

እባክዎን ማንኛቸውም ጥያቄዎች ወይም ስጋቶች ካሉዎት እንክብካቤ ሰጪዎን ያነጋግሩ።