ለኮቪድ 19 ምርመራ የክትትል መመሪያዎች

ይህ ወቅት በጣም አስፈሪ ግዜ መሆኑን እንረዳለን፡፡ በዚህ ሂደት ውስጥ ልንረዳዎት እንፈልጋለን፡፡

ውጤቱ የሚደርሰኝ መቸ ነው?

ምንም እንኳ የምርመራ ውጤቱ በአጭር ግዜ ውስጥ ቢጠናቀቅም የምርመራ ውጤቱን ለማግኘት ከ 1 እስከ 2 ቀናት ድረስ ይወስድበዎታል፡፡

እባክዎን ለምርመራ ውጤት ብለው ወደ ድንገተኛ ህክምና ክፍል&ወደ ክሊኒክ ወይም ወደ ላቦራቶሪ ክፍል አይደውሉ፡፡

ዉጤቱ የሚገለፅልኝ እንዴት ነው?

ውጤቱ ፖዘቲቭ ወይም ውሳኔ-አልባ ከሆነ

ለቀጣይ ውይይት የዋሽንግተን ዩኒቨርስቲ ህክምና አባል ይደውልለወታል፡፡

ዉጤትዎን ኢ-ኬር ወይም QR ኮድን ተጠቅመው ማወቅም ይችላሉ፡፡

ውጤቱ ኔጌቲቭ ከሆነ

ይህ መረጃ በስልክ&በኢ-ኬር ወይም በ QR ኮድ ይላክልዎታል፡፡

ቅድመ ቀዶ-ጥገና ግምገማ፡- የቀዶ-ጥገና ቡድን አባል የሆነ ሰው ውጤቱን በድጋሜ ያየውና አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ ያናግርዎታል፡፡የኮቪድ-19 የተጋላጭነት አደጋን ለመቀነስ እባክዎን የቀዶ-ጥገና ቀንዎ እስኪደርስ ድረስ እራስዎን ለይተው /አግልለው ያቆዩ፡፡

ኢ-ኬር፡- ዉጤትዎን በፍጥነት ለማግኘት ፈጣኑ መንገድ ይህ ነው፡፡ ዉጤቶች ወደ ኢ-ኬር የሚላኩት ወደ mychart.uwmedicine.org ሲሆን ዉጤቶች በተጠናቀቁና ወደ ሲስተማችን በተላኩ በ 1 ሰአት ውስጥ ነው፡፡ እኛ እርስዎን ከማግኘታችን በፊትም ዉጤትዎን ቀድመው ሊያገኙ ይችላሉ፡፡

QR ኮድ፡-የ QR ኮድ ያለበት ብጣሽ ወረቀት(ላብል) ተሰጥተው ከሆነ ዉጤትዎን በ securelink.labmed.uw.edu አማካኝነት ማየት ይችላሉ፡፡ የምርመራው ውጤት መጠናቀቁንና ለእይታ ዝግጁ መሆኑን የሚገልፅ ማስታወሻ አይላክልዎትም፡፡ ነገር ግን ድረ-ገፁን የቻሉትን ያክል ግዜ ደጋግመው በመክፈት እና በማየት የምርመራው ውጤት ምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ማየት ይችላሉ፡፡

ሰቲከር(ተለጣፊ ወረቀት) እዚህ ቦታ ላይ ከሌለ የርስዎ የምርመራ ዉጤት ማያ QR ኮድ አይደለም፡፡

የምርመራ ዉጤትን በመጠባበቅ ላይ እያለሁ ምን ማድረግ ይጠበቅብኛል?

ወደ ስራ አይመለሱ፤ የተለመዱ የቤት-ዉጭ እንቅስቃሴዎችን አያከናውኑ፡፡ የህክምና እንክብካቤ ለማግኘት ካልሆ በስተቀር ወደ ውጭ አይውጡ/ቤት ይቀመጡ፡፡ በጀርባ ገፅ የተመለከቱትን ራስን የማግለል መመሪያወዎች ይተግብሩ፡፡

ለጥያቄ ማንን ማናገር እችላለሁ ?

ለማንኛውም የኮቪድ-19 ነክ ጥያቄዎች እና ምልክቶች እየተባባሱ ከመከጡብዎት በ206.520.8700 ይደውሉ፡፡ ለምርመራ ውጤት ብለው እኛን ከማናገርዎ በፊት እባክዎን 48 ሰአታትን ይጠብቁ፡፡

የምርመራ ውጤቴ ……… ከሆነ ምን ማድረግ ይኖርብኛል?


የእርስዎ ምርመራ ውጤት ፖዘቲቭ (በሽታው ያለበት) ከሆነ ይህ ማለት የኮቪድ-19 በሽታ አምጭ ተህዋስ ኖቬል ኮሮና ቫይረስ(ሳርስ-ኮቭ-2፡- SARS-CoV-2) በወሰድነው የደም ናሙና ውስጥ አለ ማለት ነው፡፡ የኮቪድ-19 በሽታ ህክምና አንቲባዮቲክን አይፈልግም፡፡ በአጠቃላይ የእርስዎ ምልክቶች ቀለል ያሉና ወጥ ከሆኑ እባክዎን በቤትዎ ውስጥ ራስዎን ከሌሎች ሰዎች ያግልሉ፡፡ ለመተንፈስ ከተቸገሩ ግን በፍጥነት ዶክተርዎን ያናግሩ፡፡ምርመራ ያደረጉት ለቅድመ ቀዶ-ጥገና መደበኛ ምርመራ አካል ከሆነ የቀዶ-ጥገናዎ ቡድን አባል ያናግርዎታል፡፡

ቀጣይ ደረጃዎች

 • የህክምና እንክብካቤ ለማግኘት ካልሆ በስተቀር ወደ ውጭ አይውጡ/ቤት ይቀመጡ
 • ቤትዎ ውስጥ ራስን በማግለል ረገድ ቀጥለው የቀረቡትን መመሪያዎች ይተግብሩ፡፡
 • ዶክተርዎን ወይም ሆስፒታልዎን ከመጎብኘትዎ በፊት ቀድመው ይደውሉ፡፡

በቤት ውስጥ ራስን የማግለሉ ሂደት መቸ ሊያቆም ይችላል?

እራስዎን ማግለል ይኖርበዎታል፡

 • ቢያንስ ለ 10 ቀናት እና፡፡
 • የትኩሳት ማብረጃ መድሃኒት ሳይወስዱ የመጨረሻው ትኩሳት ከተሰማዎት ቢንስ 24 ሰአት እስኪሞላው ድረስ እንዲሁም፡፡
 • ሌሎች ምልክቶች መሻሻል እስኪያሳዩ ድረስ፡፡


የእርስዎ የምርመራ ውጤት ውሳኔ-አልባ ከሆነ ይህ ማለት የኮቪድ-19 በሽታ አምጭ ተህዋስ ኖቬል ኮሮና ቫይረስ(ሳርስ-ኮቭ- 2) በወሰድነው የደም ናሙና ውስጥ ሊኖር ይችላል ማለት ነው፡፡.የውሳኔ-አልባ የምርመራ ውጤት ህክምናው ልክ እንደ ፖዘቲቭ የምርመራ ውጤት ህክምና ነው፡፡


ዉጤትዎ ነጌቲቭ(በሽታው ያልተገኘበት) ከሆነ ኮቪድ-19 አለበዎት ማለት አይደለም፡፡ የተለመደውን ጉንፋን አካቶ በርካታ የመተንፈሻ አካላት ቫይረሶች እርስዎ ያለብዎትን ምልክቶች ሊያስከትሉ ይችላሉ፡፡ምርመራ የሚደረግልዎት ለመደበኛው የቅድመ ቀዶ-ጥገና ምርመራ ከሆነ እና አሰፈላጊ ከሆነ የቀዶ-ጥገና ሃኪም ቡድን አባል ያነጋግረዎታል፡፡

ቀጣይ ደረጃዎች፡-

 • ከታመሙ ቤትዎ ውስጥ ይቀመጡ፡፡
 • ምልክቶቹዎን ይከታተሉ፤ እየተባባሱ ከሄዱ ለዶክተርዎ ይንገሩ፡፡
 • ጥያቄ ካለዎት ዶክተርዎን ያነጋግሩ፡፡

በቤት ውስጥ ራስን የማግለሉ ሂደት መቸ ሊያቆም ይችላል?

ምልክቶቹ እስካሉብዎት ድረስ በሽውታውን ለሌላ ሰው ሊያስተላልፉ ይችላሉ፡፡ስለዚህ የእርስዎ ምልክቶች ሙሉ በሙሉ ከጠፉ/ከተሸሻሉ በኋላ እንኳ 24 ሰአት ሳይሞላዎ የተለመዱትን እለታዊ እንቅስቃሴዎች ማድረግና ወደ ስራዎ መመለስ አይችሉም፡፡ለምሳሌ ወደ ቀድሞ ሙሉ የጤንነት ደረጃዎ የተመለሱበት ማክሰኞ ቢሆን እስከ እሮብ ድረስ ራስዎን አግልለው መቆየት ይኖርበዎታል፡፡

ምርመራ ያደረጉት ኮቪድ-19 ካለበት የቤተሰብ አባል ጋር ለንክኪ በመጋለጥዎ ከሆነ ራስዎን ለ 14 ቀናት ኳራንቲን ማድረግ ይኖርበዎታል፡፡ የ14 ቀን የማግለል ግዜ የሚጀምረው የተጠቃው የቤተሰብዎ አባል ኳራንቲን ከተደረገበት ግዜ ጀምሮ ነው፡፡ እራስዎን ከተጠቃው የቤተሰብዎ አባል ማግለል/ኳራንቲን ማድረግ ካልቻሉ የ14 ቀኑ የማግለል ግዜ የሚጀምረው ታካሚው ራስ የማግለሉን ሂደት ለማቋረጥ መስፈርቱን ሲያሟላ ይሆናል፡፡

የቤት ውስጥ ራስን የማግለል መመሪያዎች

የበሽታውን ስርጭት ለመቀነስ ቤትዎ ውስጥ እንዲቀመጡ እና ከሌሎች ሰዎች ጋር ያለዎትን ንክኪ እንዲቀንሱ እንመክራለን፡፡

ለህክምና አገልግሎት ካልሆነ በቀር ከቤትዎ አይውጡ፡- ወደ ስራ &ት/ቤት ወይም ህዝብ ወደሚሰባሰብባቸው ቦታወች አይሂዱ& የህዝብ &የደባል(ራይድ ሼር) እና የታክሲ መጓጓዣዎችን አይጠቀሙ፡፡

በተቻለ መጠን ቤትዎ ውስጥ ከሚገኙ ሌሎች ሰዎች ራስዎን ያግልሉ፡፡- በቤትዎ ውስጥ በተቻለ መጠን በልዩ የግል ክፍልዎ ውሰጥ በመቀመጥ ራስዎን ከሌሎች ሰዎች ለማራቅ/ለማግለል ይሞክሩ፡፡የሚቻል ከሆነም የግልዎን/የተለየ መፀዳጃ ይጠቀሙ፡፡

ሁልግዜ እጅዎን ያፅዱ፡-ሁልግዜ እጅዎን በሳሙና እና በውሃ ቢያንስ ለ20 ሴኮንዶች በመፈተግ ይታጠቡ፡፡ ውሃ እና ሳሙና ከሌለ እጆችዎን የአልኮል ይዘት ባለው የእጅ ማፅጃ(ሳኒታይዘር) የእጅዎን ሁሉንም ስፍራዎች በማዳረስ እስኪደርቅ ድረስ ያፋትጉት፡፡ ባልታጠቡ እጆች አይንን &አፍንጫንና አፍን ከመንካት ይቆጠቡ፡፡

የቤት ቁሳቁሶችን ቤት ውስጥ ካሉ ሌሎች ሰዎች ጋር አይጋሩ፡- ይህ የሚያካትተው ድስቶችን &የውሀ መጠጫዎችን&ኩባያዎችን&የመመገቢያ እቃዎችን&ፎጣዎችን ወይም አልጋዎች መጋራትን ነው፡፡ እነኝህን እቃዎች ከተጠቀሙባቸው በኋላ በውሃ እና በሳሙና በደንብ ይጠቧቸው፡፡

ዘውትር “በከፍተኛ ደረጃ የሚነኩ” ቦታዎችን ያፅዱ፡- ይህ የሚያካትተው ቆጣሪዎችን & የጠረጴዛ ላይ ጣውላዎችን &የበር እጀታዎችን &የሻወር ተገጣሚዎችን &መፀዳጃ ቤቶችን &ስልኮችን&የመተየቢያ ቦርዶችን&ታብሌቶችን እና የአልጋ-ጎን ጠረጴዛዎችን ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ደም&ሰገራ ወይም ከሰውነት የሚወጣ ፈሳሽ ሊኖርበት የሚችለውን ማንኛውንም ስፍራ ያፅዱ፡፡ የአጠቃቀም መመሪያው ላይ በተገለፀው መሰረት የቤት ውስጥ ማፅጃ መወልወያ(ዋይፕ) ወይም የሚረጭ ስፕሬይ ይጠቀሙ፡፡

ሲያስልዎ እና ሲያስነጥስዎ በሶፍት&በፊት መሸፈኛ ጭምብል አለያም በክርንዎ ይሸፍኑ፡- የተጠቀሙበትን ሶፍት ወደ የረጠቡ ቆሻሻ ማጠራቀሚያ ገንዳ ይጨምሩ፤ ወዲያዉኑ እጆችዎን በሳሙና እና በውሃ ቢያንስ ለ20 ሴኮንድ ያክል በመፈተግ ይታጠቡ አለያም 60% የአልኮል ይዘት ባለው የአልኮል-ነክ የእጅ ማፅጃ(ሳኒታይዘር) ያፅዱ፡፡ እጆች በሚታዩ መልኩ ከቆሸሹ ግን የግድ በሳሙና እና በውሃ መታጠብ ይኖርባቸዋል፡፡

የጤና እንክብካቤ ከጤና ተቋም ሲፈልጉ፡-

 • ህመምዎ እየተባባሰ ከሄደ(ለምሳሌ ለመተንፈስ ከተቸገሩ) ወዲያውኑ የህክምና ክትትል ያድርጉ፡፡
 • ከተቻለ የጤና እንክብካቤ አቅራቢዎ ከመድረስዎ በፊት ቀድመው ይደውሉ፡፡
 • ወደ ጤና ተቋሙ ከመግባትዎ በፊት የፊት መሸፈኛ ጭንብል ያጥልቁ፡፡
 • ቢቻል አምቡላንሱ ወይም የአስቸኳይ ህክምና ድጋፍ አድራጊዎቹ ወደ እርስዎ ከመድረሳቸው በፊት የፊት መሸፈኛ ጭንብል ያጥልቁ፡፡
 • እነዚህ ደረጃዎች ሌሎች ሰዎች ለበሽታው እንዳይጋለጡ እና እንዳይያዙ የጤና አቅራቢ ቢሮዎ እንዲከላከል ያግዙታል፡፡

ምንጮች

የዋሽንግተን ዩኒቨርስቲ ህክምና ኮቪድ-19 መረጃ
uwmedicine.org/coronavirus

የዋሽንግተን ግዛት የጤና ዲፓርትመንት 
doh.wa.gov/Portals/1/Documents/1600/coronavirus/COVID-19-Factsheet-amharic.pdf

የበሽታዎች መከላከያ እና ቁጥጥር ማእክል
cdc.gov/coronavirus/2019-ncov/faq.html

ከታመሙ ማድርግ ያለበዎትን በተመለከተ
cdc.gov/coronavirus/2019-ncov/if-you-are-sick/steps-when-sick.html

የመረጃ ስልኮች/መስመሮች

በዋሽንግተን ግዛት የጤና ዲፓርትመንት የኮቪድ-19 የጥሪ ማዕከል
1.800.525.0127

የዋሽንግተን ዩኒቨርስቲ ህክምና የኮቪድ-19 መረጃ መስመር
206.520.2285