ኢንፍሉዌዛን (ፍሉን) መከላከል ላይ ትኩረት አድርጉ

ስለ 2020-21 ኢንፍሉዌዛ(ፍሉ)ወቅት

የኢንፍሉዌዛን(ፍሉ) ክትባት መከተብ ከመቼውም ጊዜ ይበልጥ አስፈላጊ ነው። እርስዎ እና የሚወዷቸውን ሰዎች ጤና ለጠበቅ ብቻ ሳይሆን ፣ በኮቪድ-19(COVID-19) ወረርሽኝ ወቅት የሕመምን ስርጭት ለመቀነስ እና የጤና እንክብካቤ ሀብቶችን ለመቆጠብ ጭምር ነው።

የኢንፍሉዌዛን (ፍሉ)ክትባትዎን እንዴት እንደሚከተቡ

የኢንፍሉዌዛ (ፍሉ) ክትባት ቀጠሮ ያስይዙ

አብዛኞቹ የሁልጊዜ ሕክምና ሰጪ ክሊኒኮች ጋ በኢኬር (MyChart) ድረገጽ ቀጠሮ ያስይዙ  ወይም 206.520.5000 ይደውሉ።

አስቀድመው ከልዩ ሕክምና ሰጪ ባለሙያዎ ጋር ቀጠሮ ይዘው ከሆነ የኢንፍሉዌዛን(ፍሉ)ክትባት እንዲከተቡ ይጠይቁ ፡፡

 

የአስቸኳይ እንክብካቤ ክሊኒክ ጋ ይሂዱ

የኢንፍሉዌዛ(ፍሉ) ክትባቶች በሳምንት ሰባት ቀናት በዋሽንግተን ዩኒቨርስቲ ሕክምና አስቸኳይ እንክብካቤ (UW Medicine Urgent Care) ያገኛሉ ፡፡ ለዕለት ቀጠሮ በቀላሉ በድረገጽ ላይ ይመዝግቡ ፡፡ አዲስ ሕመምተኞች እንቀበላለን፡

መድኃኒት ቤት (ፈርማሲ) ይሂዱ

በአቅራቢያዎ ያለ የኢንፍሉዌዛ (ፍሉ) ክትባት የሚሰጥ መድኃኒት ቤት(ፈርማሲ)ይሂዱ ፡፡ 

ስለ ኢንፍሉዌዛን (ፍሉ) ክትባት መረጃ


የበሽታ ቁጥጥር እና መከላከያ ማዕከላት (ሲ.ዲ.ሲ-CDC) እድሜያቸው ከ 6 ወር እና ከዚያ በላይ ለሆኑ ሁሉ ልዩ ሁኔታ ከሌለ በስተቀር ዓመታዊ ክትባት እንዲከተቡ ይመክራሉ ።

ክትባቱ በተለይ ለከባድ ኢንፍሉዌዛን(ፍሉ)ከፍተኛ ችግር የመጋለጥ ዕድል ላላቸው ሰዎች አስፈላጊ ነው ።

ዕድሜያቸው ከ 6 ወር እስከ 8 ዓመት የሆኑ ሕፃናት በአንድ ኢንፍሉዌዛን (ፍሉ) ወቅት ሁለት ጊዜ ክትባት ሊያስፈልጋቸው ይችል ይሆናል። ሌላው ሰው በእያንዳንዱ ኢንፍሉዌዛን (ፍሉ) ወቅት አንድ ክትባት ብቻ ያስፈልጋቸዋል ።


እስከ ጥቅምት (October) ወር መጨረሻ ድረስ መከተቡ ጥሩ ሀሳብ ነው።  በአሜሪካ ውስጥ የኢንፍሉዌዛ(ፍሉ) ወቅት ከህዳር ግማሽ እስከ መጋቢት ግማሽ (ከኖቬምበር እስከ ማርች- November and March) ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሳል እናም እርስዎን የሚከላከሉ ፀረበሽታ አካላትን ለመፍጠር ሰውነትዎ እስከ ሁለት ሳምንታት ይፈጅበታል ፡፡


የክትባት ውጤታማነት ከዓመት ወደ ዓመት ሊለያይ ቢችልም ፣ የበሽታ ቁጥጥር እና መከላከያ ማዕከላት (ሲዲሲ-CDC) ያወጡት የቅርብ ጊዜ ጥናት ሪፖርት የኢንፍሉዌዛን (ፍሉ) ክትባት በጠቅላላው ህዝብ መካከል ከ 40% እስከ 60% የሚሆነውን የኢንፍሉዌዛ (ፍሉ) በሽታ ተጋላጭነትን ዕድል ሲቀንሰው አብዛኛው ከሚዘዋወረውን የኢንፍሉዌዛ (ፍሉ) ቫይረስ ጋር የኢንፍሉዌዛ (ፍሉ) ክትባት በጥሩ ሁኔታ ተዛምዷል

የዚህ ዓመት የኢንፍሉዌዛ(ፍሉ) ክትባት ውጤታማ መሆኑን እስከ ኢንፍሉዌዛን(ፍሉ) ወቅት መጨረሻ ድረስ ስለማናውቅ ፤ እራስዎን እና ህብረተሰቡን ለመጠበቅ ማድረግ የሚችሉት ከሁሉ የተሻለው ነገር የኢንፍሉዌዛን (ፍሉን) ክትባት መከተብ ነው።፡


የክትባት ውጤታማነት ከዓመት ወደ ዓመት ሊለያይ ቢችልም ፣ የበሽታ ቁጥጥር እና መከላከያ ማዕከላት (ሲዲሲ-CDC) ያወጡት የቅርብ ጊዜ ጥናት ሪፖርት የኢንፍሉዌዛን (ፍሉ) ክትባት በጠቅላላው ህዝብ መካከል ከ 40% እስከ 60% የሚሆነውን የኢንፍሉዌዛ (ፍሉ) በሽታ ተጋላጭነትን ዕድል ሲቀንሰው አብዛኛው ከሚዘዋወረውን የኢንፍሉዌዛ (ፍሉ) ቫይረስ ጋር የኢንፍሉዌዛ (ፍሉ) ክትባት በጥሩ ሁኔታ ተዛምዷል

የዚህ ዓመት የኢንፍሉዌዛ(ፍሉ) ክትባት ውጤታማ መሆኑን እስከ ኢንፍሉዌዛን(ፍሉ) ወቅት መጨረሻ ድረስ ስለማናውቅ ፤ እራስዎን እና ህብረተሰቡን ለመጠበቅ ማድረግ የሚችሉት ከሁሉ የተሻለው ነገር የኢንፍሉዌዛን (ፍሉን) ክትባት መከተብ ነው።፡


የለም። የኢንፍሉዌዛ(ፍሉ) ክትባቶች የኢንፍሉዌዛ(ፍሉ)በሽታ ሊያስከትሉ አይችሉም ፡፡ ከበሽታ ቁጥጥር እና መከላከያ ማዕከላት (ሲዲሲ-CDC) ስለ ኢንፍሉዌዛን(ፍሉ) ክትባት እንዴት እንደሚሠራ የበለጠ ይረዱ።


አዎ። በእያንዳንዱ የዋሽንግተን ዩኒቨርስቲ ሕክምና ሆስፒታል እና ክሊኒክ ቅድሚያ የምንሰጠው ለእርስዎ ደህንነት ነው። የእርስዎን የኢንፍሉዌዛ(ፍሉ) ክትባት የበለጠ ደህንነቱ የተጠበቀ እንዲሆን በግዴታ ጭምብል በማድረግ ፣ አካላዊ ርቀቶች በመጠበቅ ፣ የሠራተኞች የግዴታ ምርመራ እና ሌሎችንም አድርገናል።  


ጤናማ እና ዕድሜያቸው ከ 2 እስከ 49 ዓመት ለሆኑ ሰዎች በአፍንጫ የሚረጨው የኢንፍሉዌዛ(ፍሌ)ክትባት(የተዳከመ የኢንፍሉዌንዛ ክትባት ወይም ፍሉሚስት- FluMist )አማራጭ ነው። ነፍሰ ጡር ሴቶች እና ከ 2 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናት በአፍንጫ የሚሰጠውን ክትባት መውሰድ የለባቸውም ።  በተጨማሪ የበሽታ ቁጥጥር እና መከላከያ ማዕከላት (ሲዲሲ-CDC)የተወሰኑ መሰረታዊ የጤና ሁኔታዎች ላላቸው ሰዎች የጥንቃቄ እርምጃዎችን ይዘረዝራል ፡


አዎ ኢንፍሉዌዛ(ፍሉ) ለብዙ ሰዎች በተለይም ከ 65 ዓመት በላይ ለሆኑ ፣ ለትንንሽ ሕፃናት እና እንደ ስኳር በሽታ ወይም የልብ በሽታ ያሉ ነባር የጤና እክሎች ላላቸው ሰዎች አደገኛ ነው ፡፡ ነፍሰ ጡር ሴቶችም ለኢንፍሉዌዛ(ፍሉ) ችግሮች ከፍተኛ ተጋላጭ ናቸው ፡፡ ሆኖም ኢንፍሉዌዛ(ፍሉ) ማንንም ሰው እንዲታመም እና በሆስፒታል እስከመተኛት ሊያደርስ እንደሚችል መገንዘብ ጠቃሚ ነው ፤ እናም እያንዳንዱ የኢንፍሉዌዛ(ፍሉ) ወቅት በሁሉም ዕድሜ ክልል ውስጥ ላሉ ከኢንፍሉዌዛ(ከፍሉ)ጋር የተያያዘ ሞት ያስከትላል ፡፡


የፊት መሸፈኛ ማድረግ እና አካላዊ ርቀት በመሳሰሉ የመከላከያ እርምጃዎችም ቢሆን የኢንፍሉዌዛ(ፍሉ) ስርጭት አሁንም በአካባቢያችን ውስጥ ይገኛል። ክትባት መከተቡ የኢንፍሉዌዛ(ፍሉ) መስፋፋትን የሚገድብ ሲሆን ይህም ሆስፒታል መተኛት እና መሞትን የሚቀንስ እና COVID-19 ላላቸው ሰዎች እንክብካቤ የሚያደረግበትን መጠናቸው አነስተኛ የሆኑትን የሕክምና ሀብቶች ይቆጥባል ፡፡


ኢንፍሉዌዛን(ፍሉን)ለመከላከል የተሻለ መንገድ ክትባት በየዓመቱ መከተብ ነው። የታመሙ ሰዎችን ማግለል ፣ ሳልዎን መሸፈን እና እጅዎን መታጠብ የመሳሰሉት ጥሩ የጤና ልምዶች የጀርም ስርጭትን ለማስቆም እንዲሁም እንደ ኢንፍሉዌዛ(ፍሉ) ያሉ የመተንፈሻ አካላት በሽታዎችን ለመከላከል ይረዳሉ ፡፡  


የክትባት እጥረት አለ የሚል ምንም አልሰማንም 

የይዘት ትኩረት

የኢንፍሉዌዛ(ፍሉ) እና የኮቪድ-19 ( Covid-19) ሕመም ምልክቶች


በወረርሽኙ ወቅት የኢንፍሉዌዛ(ፍሉ) ክትባት መከተብ በጣም አስፈላጊ ነው ምክንያቱም የኢንፍሉዌዛ(ፍሉ) ክትባቶች የኢንፍሉዌዛን(ፍሉ) በሽታዎችን ፣ ሆስፒታል መተኛት እና በጤና አጠባበቅ ስርዓት ላይ የሞትን ጫና ስለሚቀንሱ ኮቪድ-19 (COVID-19) ላላቸው ሰዎች እንክብካቤ የሚያስፈልጉ የሕክምና ሀብቶች ይቆጥባሉ ፡፡ በተጨማሪም ለኢንፍሉዌዛ(ፍሉ) መከተብ ሁለቱን የመተንፈሻ ላይ ቫይረሶች ችግር በአንድ ጊዜ ለመዋጋት ከመሞከር ሊያግድዎ ይችላል ፣ ከታመሙም ሐኪምዎ በተሻለ እንዲረዳዎ ያስችለዋል ፡፡

የኢንፍሉዌዛ(ፍሉ) እና የ COVID-19 ምልክቶች በጣም ተመሳሳይ ሊሆኑ ስለሚችሉ የኢንፍሉዌዛ(ፍሉ) በሽታ ያለባቸው ሰዎች ለሁለቱም ኢንፌክሽኖች መመርመር ይኖርባቸዋል። በቤት ውስጥ የሕመም ስሜት ምልክቶቻቸውን በሚያስተዳድሩ ጤናማ ጎልማሶች ላይ የኢንፍሉዌዛ(ፍሉ)በሽታ መመርመር ሁልጊዜ ባያስፈልገንም አሁንም የCOVID-19 ሕመም ምልክቶች ያላቸውን ሁሉ መመርመር በጣም አስፈላጊ ነው ፡፡


እስካሁን በተማርናቸው ነገሮች ሁሉ ላይ በመመርኮዝ በሕመም ምልክቶች ላይ ብቻ በኢንፍሉዌንዛ እና በኮቪድ-19 (COVID-19) መካከል ያለውን ልዩነት ለመለየት ፈጽሞ የማይቻል ነው ፡፡

የኮቪድ-19 (COVID-19) እና የኢንፍሉዌዛን(ፍሉ)ሕመም ምልክቶች ከመለስተኛ እስከ ከባድ ሊደርሱ ይችላሉ ።

COVID-19 እና ኢፍሉዌዛ(ፍሉ)ያላቸው የጋራ ምልክቶች፦ 

 • ትኩሳት ወይም ትኩሳት / ብርድ ብርድ ማለት
 • ሳል
 • የትንፋሽ እጥረት ወይም ለመተንፈስ መቸግር
 • ድካም (መዳካም)
 • የጉሮሮ መቁሰል
 • የአፍንጫ ፍሳሽ ወይም የአፍንጫ መታፈን
 • የጡንቻ ህመም ወይም የሰውነት ህመም
 • ራስ ምታት
 • ምንም እንኳን ይህ በልጆች ላይ ከአዋቂዎች የበለጠ የተለመደ ቢሆንም አንዳንድ ሰዎች ማስታወክ እና ተቅማጥ ሊኖራቸው ይችላል

ከኢንፍሉዌዛ(ፍሉ) በተቃራኒ የኮቪድ-19 (COVID-19 ሕመም ምልክቶች ጣዕምን ወይም ማሽተትን አቅም ማጣት ሊያካትቱ ይችላሉ

ከሁሉ የተሻለው መንገድ ለኢፍሉዌዛ(ፍሉ) እና ለኮቪድ-19 (COVID-19) በሽታ ለማረጋገጥ ምርመራ ማድረግ ነው ።


አዎ ፣ ኢንፍሉዌዛ(ፍሉ) እና ኮቪድ-19 (COVID-19)ንን በተመሳሳይ ጊዜ ሊይዝ ይቻላል ፡፡ እኛ ምን ያህል ጊዜ እንደሚከሰት ወይም ሁለቱ ቫይረሶች እንዴት እንደሚገናኙ አናውቅም ፤ ግን ከሁለቱም ቫይረሶች ጋር በአንድ ጊዜ መበከል ከአንድ ብቻ ከመበከል የበለጠ አደገኛ ይሆናል ፡፡


ኢንፍሉዌዛን(ፍሉ)ወይም ኮቪድ-19ን (COVID-19) የሚመስሉ የበሽታ ምልክቶች ያለብዎ ከሆነ ከጤና እንክብካቤ ሰጪዎት ጋር ተማከሩ።  ዋሽንግተን ዩኒቨርስቲ ሕክምና (UW Medicine) ውስጥ የሚከተሉትን ማድረግ ይችላሉ፦

 • መመሪያ ለማግኘት ሐኪምዎ ጋ ይደውሉ እና ሕመም ምልክቶችዎን ይከታተሉ። ሐኪምዎን በስልክ ወይም በኢኬር (MyChart) ማግኘት ይችላሉ 
 • በማንኛውም ጊዜ 24 ሰዓት 7ቱንም ቀናት የዋሽንግተን ዩኒቨርስቲ ሕክምናን (UW Medicine) ምናባዊ (virtual) ክሊኒክን በመጠቀም እንክብካቤ ያግኙ ፡