የፋይናንስ እርዳታ ፖሊሲ – በግልጽ ቋንቋ የተጻፈ አጭር ዝርዝር

የሚቀርብ የፋይናንስ ድጋፍ: የሚሰጠው የገንዘብ እርዳታ፡ UW Medicine ባለው የፋይናንስ እርዳታ ፖሊሲ መሠረት፣ ለድንገተኛ ሕክምና ወይም ለሌላ በሕክምና አስፈላጊ ለሆነ እንክብካቤ መክፈል ለማይችሉ ብቁ ታካሚዎች የፋይናንስ እርዳታ ይሰጣል። የ UW Medicine ን የሚመርጡ ታካሚዎች፣ ካለን ልምድ፣ ሞያና ባለው በጣም ዘመናዊ በሆነው የሕክምና እንክብካቤ፣ ሁሉንም ባንድ የጤና ጥበቃ ጥላ ሥር ማግኘት ይችላሉ። “UW Medicine”፣ የሚከተሉትን Airlift Northwest, Harborview የህክምና ማዕከል ፣ UW የህክምና ማዕከል ፣ Northwest ሆስፒታል እና የህክምና ማዕከል ፣ UW ሐኪሞች፣ UW የአጎራባች ክሊኒኮች፣ እና Valley የህክምና ማዕከልን ያካተተ ነው።

የብቁነት መስፈርቶችና የሚቀርብ ድጋፍ: የብቁነት መስፈርቶች እና የቀረበው ድጋፍ፡ ለገንዘብ እርዳታ ብቁ መሆን በበርካታ ሁኔታዎች ላይ የተመሰረተ ነው። እነዚህም የሚፈለገው እንክብካቤ አይነት፣የኢንሹራንስ(መድህን) ሽፋን ወይም ሌላ የክፍያ ምንጭ፣ገቢ፣ የቤተሰብ መጠን፣ ንብረት፣የዋሽንግቶን ስቴት ነዋሪነት፣ ታካሚው ወይም ሃኪሙ ሊጠቃለል ይገባል የሚሉት ልዩ ትኩረት።

የፋይናንስ እርዳታ የሚጠይቁ ታካሚዎች የሚከተሉትንም ጨምሮ የፋይናንስ እርዳታ ማመልከቻ ሂደትን መከተል አለባቸው። ይህ የታካሚ የW-2 መግለጫ፣ የወቅታዊ ክፍያ ጉራጆች፣ የባንክ መግለጫዎች ወይም ያለፈው አመት የገቢ ግብር ተመላሽ ማቅረብን እና በግዛት ድጎማ የሚደረግበት እንክብካቤን (Medicaid) ጨምሮ ለሁሉም የሚቀርቡ የድጋፍ ምንጮች የማመልከቻ ሂደቱን ሞልቶ ማጠናቀቅን ያጠቃልላል።

ለድጋፍ እንዴት ማመልከቻ እንደሚቀርብ እና ምን ለድጋፍ ብቁ እንደሆነ: ታካሚው ወይም ማንኛውም በታካሚው እንክብካቤ የሚያገባው ሰው፣ የቤተሰብ አባልና አገልግሎት ሰጪውን ጨምሮ በማንኛውም ሰአት ሰለታካሚው የገንዘብ ችግር ማንሳት ይችላሉ። ታካሚው ወይም ኃላፊነት ያለበት ወገን የፋይናንስ እርዳታ ማመልከቻ እንዲሞላ ይበረታታል። ለፋይናንስ እርዳታ ብቁ ለመሆን፣ ለሒሳቡ የፍርድ ቤት ትዛዝ ከመደረሱ በፊት በማንኛውም ግዜ ላይ ማመልከቻ ማስገባት ይቻላል።

የፋይናንስ እርዳታው የሚወሰነው በ UW Medicine ቦታዎች በ UW የሕክምና ባልደረቦች ለተሰጡ የሕክምና እንክብካቤዎች ብቻ ነው። እንደ የመጓጓዣ፣ የምግብ፣ የማረፊያ ቦታና ለዘላቂ የሕክምና መሳሪያዎች ወጪዎች የመሳሰሉት በፋይናንስ ድጋፍ ስር አይሸፈኑም።

ቅጂዎች ከየት እንደሚገኙ፣ ሰነዶች የት እንደሚገቡ እና የግንኙነት መረጃ: የUW Medicine የገንዘብ ድጋፍ ፖሊሲ፣ የገንዘብ ድጋፍ ማመልከቻ፣ በግልጽ ቋንቋ የተጻፈ አጭር ዝርዝር፣ እና የሂሳብ አከፋፈል እና ስብስብ መመሪያዎች ያለክፍያ በነጻ ማግኘት ይቻላል። እነዚህን ሰነዶች በተለያዩ ቋንቋዎች በኢንተርኔት፣ በስልክ ወይም በአካል ተገኝተው ማግኘት ይችላሉ። ሰነዶችን በኦንላይን ከ uwmedicine.org/financialassistance ወይም valleymed.org/financialassistance. ማውረድ ወይም ፕሪንት ማድረግ ይቻላል። እንክብካቤ ለሚያገኙበት ቦታ በመደወል ኮፒዎን መጠየቅ ይችላሉ። ግልባጮቹን በአካል፣ በ UW Medicine የሐኪም ቤት ቦታዎች ውስጥ ባሉ የታካሚ መቀበያዎች እና የድንገተኛ ሕክምና ክፍል (Admissions and Emergency Departments) ውስጥ ይገኛሉ።

ለእንግሊዘኛ የፋይናንስ/ገንዘብ ድጋፍ ማመልከቻ እና ደጋፊ ሰነዶች በአሁኑ ወቅት የእንክብካቤ አካባቢዎን መሰረት አድርገው ሰነዶችዎን ለማስገባት MyChartን (ከኤየርሊፍት ኖርዝዌስት በስተቀር) መጠቀም ይችላሉ። ሁሉንም ሌሎች ማመልከቻዎችን ለማስገባት በመልዕክት፣ ፋክስ ወይም በአካል ማስገባትዎን ይቀጥሉ። UW Medicine የእያንዳንዱን ታካሚ ሚስጥራዊነት እና የግል ማንነት ይጠብቃል። ለፋይናንስ/የገንዘብ ድጋፍ እንዲጤን የሚቀርብ የትኛውም መረጃ በጤና መድን ዋስትና ተዘዋዋሪነትና ተጠያቂነት ህግ/ Health Insurance Portability and Accountability Act (HIPAA) ስር ጥበቃ የሚደረግለት የጤና መረጃ ተደርጎ ይቆጠራል።

Harborview Medical Center  
UW Physicians  
UW Medicine Primary Care   
Financial Counseling  
325 9th Ave; Mail Stop 359758  
Seattle, WA 98104-2499  
ስልክ 206.744.3084  
ፋክስ 206.744.5187  
ከሰኞ-አርብ 8:00 a.m. – 4:30 p.m. ሰዐት 
mychart.uwmedicine.org

UW Medical Center – Montlake   
UW Physicians   
UW Medicine Primary Care    
Financial Counseling   
1959 NE Pacific Street; Mail Stop 356142   
Seattle, WA 98195-6142   
ስልክ 206.744.3084   
ፋክስ 206.598.1122   
ከሰኞ-አርብ 8:00 a.m. – 4:30 p.m. ሰዐት 
mychart.uwmedicine.org

UW Medical Center – Northwest 
UW Physicians 
UW Medicine Primary Care 
Financial Counseling 
1550 N 115th St 
Seattle, WA 98133-9733 
ስልክ 206.744.3084 
ፋክስ 206.598.1122 
ከሰኞ-አርብ 8:00 a.m. – 4:30 p.m. ሰዐት 
mychart.uwmedicine.org

Valley Medical Center  
Patient Financial Services  
P.O. Box 59148  
Renton, WA 98058-2148  
ስልክ 425.690.3578  
ፋክስ 425.690.9578  
ከሰኞ-አርብ 8:00 a.m. – 5:00 p.m. ሰዐት 
mychart.valleymed.org/#mychart

Valley Medical Center  
Patient Financial Services  
3600 Lind Ave SW, Suite 110  
Renton, WA 98057-4970  
ስልክ 425.690.3578  
ፋክስ 425.690.9578  
ከሰኞ-አርብ 8:00 a.m. – 5:00 p.m. ሰዐት 
mychart.valleymed.org/#mychart

Airlift Northwest 
Patient Financial Services 
6505 Perimeter Road S., Ste 200 
Seattle, WA 98108 
ስልክ 206.598.2912 
ፋክስ 206.521.1612 
ከሰኞ-አርብ 8:00 a.m. – 5:00 p.m. ሰዐት