የፋይናንስ እርዳታ ፖሊሲ – በግልጽ ቋንቋ የተጻፈ አጭር ዝርዝር

ይህንን ገፅ በአማርኛ አውርድልኝ

የሚሰጠው የገንዘብ እርዳታ፡ UW Medicine ባለው የፋይናንስ እርዳታ ፖሊሲ መሠረት፣ ለድንገተኛ ሕክምና ወይም ለሌላ በሕክምና አስፈላጊ ለሆነ እንክብካቤ መክፈል ለማይችሉ ብቁ ታካሚዎች የፋይናንስ እርዳታ ይሰጣል። UW Medicine የሚመርጡ ታካሚዎች፣ ካለን ልምድ፣ ሞያና ባለው በጣም ዘመናዊ በሆነው የሕክምና እንክብካቤ፣ ሁሉንም ባንድ የጤና ጥበቃ ጥላ ሥር ማግኘት ይችላሉ። “UW Medicine” የሚከተሉትን Airlift Northwest, Harborview የህክምና ማዕከል UW የህክምና ማዕከል Northwest ሆስፒታል እና የህክምና ማዕከል UW ሐኪሞች፣ UW የአጎራባች ክሊኒኮች፣ እና Valley የህክምና ማዕከልን ያካተተ ነው።

የብቁነት መስፈርቶች እና የቀረበው ድጋፍ ለገንዘብ እርዳታ ብቁ መሆን በበርካታ ሁኔታዎች ላይ የተመሰረተ ነው። እነዚህም የሚፈለገው እንክብካቤ አይነት፣የኢንሹራንስ(መድህን) ሽፋን ወይም ሌላ የክፍያ ምንጭ፣ገቢ፣የቤተሰብ መጠን፣ንብረት፣የዋሽንግቶን ስቴት ነዋሪነት፣ ታካሚው ወይም ሃኪሙ ሊጠቃለል ይገባል የሚሉት ልዩ ትኩረት።

የፋይናንስ እርዳታ የሚጠይቁ ታካሚዎች የሚከተሉትንም ጨምሮ የፋይናንስ እርዳታ ማመልከቻ ሂደትን መከተል አለባቸው፣ ከሚከተሉት ውስጥ አንዱን W-2 መግለጫ፣ ወቅታዊ የደሞዝ ቼክ ቀሪ ቁራጮች፣ የባንክ ሂሳብ መግለጫ ወይም ላለፈው ዓመት የገቢ ግብር ሰነድ ማቅረብ፣ እንዲሁም ሊኖሩ ስለሚችሉ ሁሉም የፋይናንስ እርዳታ ምንጮች ማመልከቻን መሟላት አለባቸው፣ እንደ Medicaid የመሳሰሉትን በመንግስት የሚደጎሙ እርዳታዎችንም ጨምሮ።

ለእርዳታ እንዴት ማመልከት እንደሚቻል ታካሚው ወይም ማንኛውም በታካሚው እንክብካቤ የሚያገባው ሰው፣ የቤተሰብ አባልና አገልግሎት ሰጪውን ጨምሮ በማንኛውም ሰአት ሰለታካሚው የገንዘብ ችግር ማንሳት ይችላሉ። ታካሚው ወይም ኃላፊነት ያለበት ወገን የፋይናንስ እርዳታ ማመልከቻ እንዲሞላ ይበረታታል። ለፋይናንስ እርዳታ ብቁ ለመሆን፣ ለሒሳቡ የፍርድ ቤት ትዛዝ ከመደረሱ በፊት በማንኛውም ግዜ ላይ ማመልከቻ ማስገባት ይቻላል።

የፋይናንስ እርዳታው የሚወሰነው UW Medicine ቦታዎች UW የሕክምና ባልደረቦች ለተሰጡ የሕክምና እንክብካቤዎች ብቻ ነው። እንደ የመጓጓዣ፣ የምግብ፣ የማረፊያ ቦታና ለዘላቂ የሕክምና መሳሪያዎች ወጪዎች የመሳሰሉት በዚህ የፋይናንስ እርዳታ ፖሊሲ ስር አይሸፈኑም።

በሐኪም የታዘዙ መድሃኒቶች UW Medicine በኩል ታዘው UW Medicine ፋርማሲ (ካለ) ከተሞሉ ሽፋን ይደረግላቸዋል። UW Medicine የእያንዳንዱን ታካሚ ምስጥርና ክርብ ይጠብቃል። Health Insurance Portability and Accountability Act (HIPAA) መሠረት ለፋይናንስ እርዳታ የሚቀርብ ማንኛውም መረጃ፣ እንደ የተጠበቀ የጤና መረጃ ሆኖ ይቆጠራል።

ግልባጮችንና መገናኛ መረጃን የት ማግኘት እንደሚቻል UW Medicine የገንዘብ ድጋፍ ፖሊሲ፣ የገንዘብ ድጋፍ  ማመልከቻ፣ በግልጽ ቋንቋ የተጻፈ አጭር ዝርዝር፣ እና የሂሳብ አከፋፈል እና ስብስብ መመሪያዎች ያለክፍያ በነጻ ማግኘት ይቻላል። እነዚህን ሰነዶች በተለያዩ ቋንቋዎች  በኢንተርኔት፣ በስልክ ወይም በአካል ተገኝተው ማግኘት ይችላሉ። ሰነዶችን ከሚከተሉት ድረገጾች ዳውንሎድና ፕሪንት ማድረግ ይችላሉ www.uwmedicine.org/financialassistance ወይም www.valleymed.org/financialassistance. እንክብካቤ የሚፈልጉበትን ቦታ በመጥራት ቅጂዎን መጠየቅ ይችላሉ ፡፡  ግልባጮቹን በአካል፣ UW Medicine የሐኪም ቤት ቦታዎች ውስጥ ባሉ የታካሚ መቀበያዎች እና የድንገተኛ ሕክምና ክፍል (Admissions and Emergency Departments) ውስጥ ይገኛ

 

Harborview Medical Center

Financial Counseling

325 9th Ave; Mail Stop 359758

Seattle, WA 98104-2499

206.744.3084

ፋክስ 206.744.5187

- 8:00 a.m.4:30 p.m.

 

Medical Center-Montlake

Financial Counseling

1959 NE Pacific Street Mail Stop 356142

Seattle, WA 98195-6142

206.744.3084

ፋክስ 206.598.1122

- 8:00 a.m. 4:30 p.m.

 

UW Medical Center-Northwest

Financial Counseling

1550 N 115th St

Seattle, WA 98133-9733

206.744.3084

- 8:00 a.m. – 4:30 p.m.

 

Harborview Medical Center
UW Medical Center

 

Patient Financial Services

 

10330 Meridian Ave. N Suite 260
Seattle, WA 98133

 

206.598.1950 ወይም 1.877.780.1121

 

ፋክስ 206.668.6469

- 8 a.m. – 4:30 p.m.

 

 

 Valley Medical Center

 

Patient Financial Services

 

3600 Lind Ave SW, Suite 110
Renton,
WA 98057-4970

 

425.690.3578

 

ፋክስ 425.690.9578

 

- 8:00 a.m. – 5:00 p.m.

 

 

UW Physicians
UW Neighborhood Clinics

Patient Accounts & Inquiry

P.O. Box 50095
S
eattle, WA 98145-5095

206.520.9300 ወይም 1.855.520.9300

ፋክስ 206.520.3200

- 9:00 a.m. – 5:00 p.m.

 

Harborview Medical Center
UW Medical Center

Patient Financial Services

P.O. Box 95459
Seattle, WA 98145-2459

206.598.1950 ወይም 1.877.780.1121

ፋክስ 206.598.2360

- 8:00 a.m. – 4:30 p.m.

Valley Medical Center

Patient Financial Services

P.O. Box 59148
Renton, WA 98058-2148

425.690.3578

ፋክስ 425.690.9578

- 8:00 a.m. – 5:00 p.m.

Airlift Northwest

Patient Financial Services

6505 Perimeter Road S., Ste 200
Seattle, WA 98108

206.598.2912

ፋክስ 206.521.1612

- 8:00 a.m. – 5:00 p.m.