የፋይናንስ እርዳታ ማመልከቻ ቅጽ መመሪያዎች

ይህ በ UW Medicine የፋይናንስ እርዳታ ማመልከቻ ነው (ደግሞ የበጎ አድራጎት እንክብካቤ ተብሎ ይታወቃል)። የዋሽንግተን ስቴት፣ ሁሉም ሐኪም ቤቶች የተወሰኑ የገቢ መስፈርቶችን ለሚያሟሉ ሰዎችና ቤተሰቦች የፋይናንስ እርዳታ እንዲያቀርቡ ያዛል። በቤተሰብዎ ብዛትና የገቢዎ መጠን መሰረት፣ የጤና የመድን ዋስትና ቢኖርዎ እንኳን፣ ለፋይናንስ እርዳታ ብቁ ሊሆኑ ይችላሉ። እርዳታ የሚሰጥዎት የፋይናንስ እርዳታ መመሪያዎችን ካሟሉ ነው፣ እሱም የቤተሰብዎ ገቢ ከፌደራል የድህነት መመዘኛ ደረጃ 300 በመቶ እኩል ወይም ከዚያ በታች መሆኑን ይጨምራል። ተጨማሪ መረጃ መጠየቅ ወይም በሚከተለው የፋይናንስ እርዳታ ድረገጻችን www.uwmedicine.org/financialassistance ወይም www.valleymed.org/financialassistance መመልከት ይችላሉ።

የፋይናንስ እርዳታ የሚሸፍነው ምንድን ነው? የሐኪም ቤት የፋይናንስ እርዳታ የሚሸፍነው በእርስዎ ብቁነት መሠረት በ UW Medicine ለሚሰጡ ተገቢ ለሆኑ የሐኪም ቤት-ውስጥ አገልግሎቶች ነው። የፋይናንስ እርዳታ፣ በሌላ ድርጅቶች የሚሰጡ አገልግሎቶችን ጨምሮ፣ ሁሉንም የጤና እንክብካቤ ወጪዎችን ላይሸፍን ይችላል።

ማመልከቻዎ ተፈጻሚ እንዲሆን ለማድረግ ያለብዎት ነገሮች፦

  • ስለ ቤተሰብዎ አጠቃላይ ወርሐዊ ገቢ (ታክስ ከመከፈሉና ተቀናሽ (ዲዳክሽ) ከመደረጉ በፊት ያለውን ገቢ) መረጃ ይስጡን
  • ስለ የቤተሰብዎ ገቢና ለሚያሳውቋቸው ንብረቶች ሰነዶችን ያቅርቡ
  • አስፈላጊ ከሆነ ተጨማሪ መረጃ አያይዘው ያቅርቡ፣ ለምሳሌ፣ ለመረጃዎ ድጋፍ የሚሆኑ ደብዳቤዎችን ያቅርቡ
  • ቅጹ ላይ ይፈርሙና ቀኑን ይጻፉ

ለእንግሊዘኛ የፋይናንስ/ገንዘብ ድጋፍ ማመልከቻ እና ደጋፊ ሰነዶች በአሁኑ ወቅት የእንክብካቤ አካባቢዎን መሰረት አድርገው ሰነዶችዎን ለማስገባት MyChartን (ከኤየርሊፍት ኖርዝዌስት በስተቀር) መጠቀም ይችላሉ። ሁሉንም ሌሎች ማመልከቻዎችን ለማስገባት በመልዕክት፣ ፋክስ ወይም በአካል ማስገባትዎን ይቀጥሉ። UW Medicine የእያንዳንዱን ታካሚ ሚስጥራዊነት እና የግል ማንነት ይጠብቃል። ለፋይናንስ/የገንዘብ ድጋፍ እንዲጤን የሚቀርብ የትኛውም መረጃ በጤና መድን ዋስትና ተዘዋዋሪነትና ተጠያቂነት ህግ/ Health Insurance Portability and Accountability Act (HIPAA) ስር ጥበቃ የሚደረግለት የጤና መረጃ ተደርጎ ይቆጠራል።

ማመልከቻዎን ለማንቀሳቀስ በህክምና መዝገብ ቁጥር/ Medical Record Number (MRN) ስር የተመዘገቡ ታካሚ መሆን አለብዎ: ለHarborview Medical Center፣ UW Medical Center - Montlake፣ UW Medical Center-Northwest፣ UW Physicians እና UW Medicine Primary Care ማመልከቻዎን ከመሙላትዎ በፊት ለመመዝገብ ለግንኙነት ማዕከል በስልክ ቁጥር 206.520.5000 ይደውሉ።

Harborview Medical Center   
UW Physicians   
UW Medicine Primary Care   
Financial Counseling   
325 9th Ave; Mail Stop 359758   
Seattle, WA 98104-2499   
ስልክ 206.744.3084   
ፋክስ 206.744.5187   
ከሰኞ-አርብ 8:00 a.m. – 4:30 p.m. ሰዐት  
mychart.uwmedicine.org

UW Medical Center &ndash Montlake  
UW Physicians  
UW Medicine Primary Care  
Financial Counseling  
1959 NE Pacific Street; Mail Stop 356142  
Seattle, WA 98195-6142  
ስልክ 206.744.3084  
ፋክስ 206.598.1122  
ከሰኞ-አርብ 8:00 a.m. – 4:30 p.m. ሰዐት 
mychart.uwmedicine.org

UW Medical Center – Northwest  
UW Physicians  
UW Medicine Primary Care  
Financial Counseling  
1550 N 115th St  
Seattle, WA 98133-9733  
ስልክ 206.744.3084  
ፋክስ 206.598.1122  
ከሰኞ-አርብ 8:00 a.m. – 4:30 p.m. ሰዐት 
mychart.uwmedicine.org

Valley Medical Center  
Patient Financial Services  
P.O. Box 59148  
Renton, WA 98058-2148  
ስልክ 425.690.3578  
ፋክስ 425.690.9578  
ከሰኞ-አርብ 8:00 a.m. – 5:00 p.m. ሰዐት 
mychart.valleymed.org/#mychart

Valley Medical Center  
Patient Financial Services  
3600 Lind Ave SW, Suite 110  
Renton, WA 98057-4970  
ስልክ 425.690.3578  
ፋክስ 425.690.9578  
ከሰኞ-አርብ 8:00 a.m. – 5:00 p.m. ሰዐት 
mychart.valleymed.org/#mychart

Airlift Northwest 
Patient Financial Services 
6505 Perimeter Road S., Ste 200 
Seattle, WA 98108 
ስልክ 206.598.2912 
ፋክስ 206.521.1612 
ከሰኞ-አርብ 8:00 a.m. – 5:00 p.m. ሰዐት