የፋይናንስ እርዳታ ማመልከቻ ቅጽ መመሪያዎች
ይህ በ UW Medicine የፋይናንስ እርዳታ ማመልከቻ ነው (ደግሞ የበጎ አድራጎት እንክብካቤ ተብሎ ይታወቃል)። የዋሽንግተን ስቴት፣ ሁሉም ሐኪም ቤቶች የተወሰኑ የገቢ መስፈርቶችን ለሚያሟሉ ሰዎችና ቤተሰቦች የፋይናንስ እርዳታ እንዲያቀርቡ ያዛል። በቤተሰብዎ ብዛትና የገቢዎ መጠን መሰረት፣ የጤና የመድን ዋስትና ቢኖርዎ እንኳን፣ ለፋይናንስ እርዳታ ብቁ ሊሆኑ ይችላሉ። እርዳታ የሚሰጥዎት የፋይናንስ እርዳታ መመሪያዎችን ካሟሉ ነው፣ እሱም የቤተሰብዎ ገቢ ከፌደራል የድህነት መመዘኛ ደረጃ 300 በመቶ እኩል ወይም ከዚያ በታች መሆኑን ይጨምራል። ተጨማሪ መረጃ መጠየቅ ወይም በሚከተለው የፋይናንስ እርዳታ ድረገጻችን uwmedicine.org/financialassistance።
ወይም valleymed.org/financialassistance መመልከት ይችላሉ።
የፋይናንስ እርዳታ የሚሸፍነው ምንድን ነው? የሐኪም ቤት የፋይናንስ እርዳታ የሚሸፍነው በእርስዎ ብቁነት መሠረት በ UW Medicine ለሚሰጡ ተገቢ ለሆኑ የሐኪም ቤት-ውስጥ አገልግሎቶች ነው። የፋይናንስ እርዳታ፣ በሌላ ድርጅቶች የሚሰጡ አገልግሎቶችን ጨምሮ፣ ሁሉንም የጤና እንክብካቤ ወጪዎችን ላይሸፍን ይችላል።
ማመልከቻዎ ተፈጻሚ እንዲሆን ለማድረግ ያለብዎት ነገሮች፦
- ስለ ቤተሰብዎ መረጃ ለእኛ መስጠት፤ በቤተሰብዎ ውስጥ ያለውን የአባላት ቁጥርን ይጻፉ (ቤተሰብ ሲባል የሚያጠቃልለው፣ አብረው የሚኖሩ የሥጋ ዘመድ፣ የጋብቻ ወይም ጉዲፈቻ ዘመድን ነው)
- ስለ ቤተሰብዎ አጠቃላይ ወርሐዊ ገቢ (ታክስ ከመከፈሉና ተቀናሽ (ዲዳክሽ) ከመደረጉ በፊት ያለውን ገቢ) መረጃ ይስጡን
- ስለ የቤተሰብዎ ገቢና ለሚያሳውቋቸው ንብረቶች ሰነዶችን ያቅርቡ
- አስፈላጊ ከሆነ ተጨማሪ መረጃ አያይዘው ያቅርቡ፣ ለምሳሌ፣ ለመረጃዎ ድጋፍ የሚሆኑ ደብዳቤዎችን ያቅርቡ
- ቅጹ ላይ ይፈርሙና ቀኑን ይጻፉ
ጥያቄዎች ካልዎትና ይህን ማመልከቻ ለማጠናቀቅ እገዛ ከፈለጉ እባክዎን እንክብካቤ የሚፈልጉትን ከዚህ በላይ ያለውን ተቋም ያነጋግሩ። ለአካል ስንክልና እና ለቋንቋ እርዳታን ጨምሮ፣ ለማንኛውም ምክንያት እርዳታ ማግኘት ይችሉ ይሆናል።ለብቁነትዎና የይግባኝ መብቶችዎ፣ የሚመለከትዎ ከሆነ፣ ለምናደርገው የመጨረሻ ውሳኔ፣ የገቢዎን ማረጋገጫ ሰነዶችን ጨምሮ፣ የተሞላው የፋይናንስ እርዳታ ማመልከቻ ከደረሰን ቀን ጀምሮ በ 14 የካላንደር ቀኖች ውስጥ እናሳውቅዎታለን። የፋይናንስ እርዳታ ማመልከቻ በማስገባትዎ፣ የፋይናንስ ግዴታዎችንና መረጃን ለማረጋገጥ የሚያስችሉንን አስፈላጊ ምርመራዎች እንድናደርግ ፈቅደውልናል ማለት ነው።
ለመርዳት እንፈልጋለን። እባክዎን ማመልከቻዎን ወዲያው ያስገቡ! መረጃዎ እስከሚደርሰን ድረስ ቢሎች ሊደርስዎ ይችሉ ይሆናል።