የፋይናንስ እርዳታ ፖሊሲ – በግልጽ ቋንቋ የተጻፈ አጭር ዝርዝር


የፋይናንስ እርዳታ ፖሊሲ – በግልጽ ቋንቋ የተጻፈ አ​ጭር ዝርዝር (PDF)​​

የሚሰጠው የፋይናንስ እርዳታ

UW Medicine ባለው የፋይናንስ እርዳታ ፖሊሲ መሠረት፣ ለድንገተኛ ሕክምና ወይም ለሌላ በሕክምና አስፈላጊ ለሆነ እንክብካቤ መክፈል ለማይችሉ ብቁ ታካሚዎች የፋይናንስ እርዳታ ይሰጣል። የ UW Medicine ን የሚመርጡ ታካሚዎች፣ ካለን ልምድ፣ ሞያና ባለው በጣም ዘመናዊ በሆነው የሕክምና እንክብካቤ፣ ሁሉንም ባንድ የጤና ጥበቃ ጥላ ሥር ማግኘት ይችላሉ። “UW Medicine”፣ የሚከተሉትን Airlift Northwest, Harborview Medical Center (HMC)፣ UW Medical Center (UWMC)፣ Northwest Hospital & Medical Center (NWH)፣ UW Physicians (UWP)፣ UW Neighborhood Clinics (UWNC)፣ እና Valley Medical Center (VMC) ያካተተ ነው።

የብቁነት መመዘኛዎች እና የሚደረግ እርዳታ

ለገንዘብ እርዳታ ብቁ መሆን በበርካታ ሁኔታዎች ላይ የተመሰረተ ነው። እነዚህም የሚፈለገው እንክብካቤ አይነት፣የኢንሹራንስ(መድህን) ሽፋን ወይም ሌላ የክፍያ ምንጭ፣ገቢ፣የቤተሰብ መጠን፣ንብረት፣የዋሽንግቶን ስቴት ነዋሪነት፣ ታካሚው ወይም ሃኪሙ ሊጠቃለል ይገባል የሚሉት ልዩ ትኩረት።

የፋይናንስ እርዳታ የሚጠይቁ ታካሚዎች የሚከተሉትንም ጨምሮ የፋይናንስ እርዳታ ማመልከቻ ሂደትን መከተል አለባቸው፣ ከሚከተሉት ውስጥ አንዱን የ W-2 መግለጫ፣ ወቅታዊ የደሞዝ ቼክ ቀሪ ቁራጮች፣ የባንክ ሂሳብ መግለጫ ወይም ላለፈው ዓመት የገቢ ግብር ሰነድ ማቅረብ፣ እንዲሁም ሊኖሩ ስለሚችሉ ሁሉም የፋይናንስ እርዳታ ምንጮች ማመልከቻን መሟላት አለባቸው፣ እንደ Medicaid የመሳሰሉትን በስቴት የሚደጎሙ እርዳታዎችንም ጨምሮ።

ለእርዳታ እንዴት እንደሚያመለከቱ

ታካሚው ወይም ማንኛውም በታካሚው እንክብካቤ የሚያገባው ሰው፣ የቤተሰብ አባልና አገልግሎት ሰጪውን ጨምሮ በማንኛውም ሰአት ሰለታካሚው የገንዘብ ችግር ማንሳት ይችላሉ። ታካሚው ወይም ኃላፊነት ያለበት ወገን የፋይናንስ እርዳታ ማመልከቻ እንዲሞላ ይበረታታል። ለፋይናንስ እርዳታ ብቁ ለመሆን፣ ለሒሳቡ የፍርድ ቤት ትዛዝ ከመደረሱ በፊት በማንኛውም ግዜ ላይ ማመልከቻ ማስገባት ይቻላል።​

የፋይናንስ እርዳታው የሚወሰነው በ UW Medicine ቦታዎች በ UW የሕክምና ባልደረቦች ለተሰጡ የሕክምና እንክብካቤዎች ብቻ ነው። እንደ የመጓጓዣ፣ የምግብ፣ የማረፊያ ቦታና ለዘላቂ የሕክምና መሳሪያዎች ወጪዎች የመሳሰሉት በዚህ የፋይናንስ እርዳታ ፖሊሲ ስር አይሸፈኑም።

በሐኪም የታዘዙ መድሃኒቶች በ UW Medicine በኩል ታዘው በ UW Medicine ፋርማሲ (ካለ) ከተሞሉ ሽፋን ይደረግላቸዋል። UW Medicine ፣ የእያንዳንዱን ታካሚ ምስጥርና ክርብ ይጠብቃል። በ Health Insurance Portability and Accountability Act (HIPAA) መሠረት ለፋይናንስ እርዳታ የሚቀርብ ማንኛውም መረጃ፣ እንደ የተጠበቀ የጤና መረጃ ሆኖ ይቆጠራል።

ግልባጮችንና መገናኛ መረጃን የት ማግኘት እንደሚቻል

የ UW Medicine የፋይናንስ እርዳታ ፖሊሲ፣ የፋይናንስ እርዳታ ማመልከቻ፣ በግልጽ ቋንቋ የተጻፈ አጭር ዝርዝር፣ እና የቢል አደራረግ እና ዕዳ ስብሰባ ፖሊሲዎችን ያለክፍያ በነጻ ማግኘት ይቻላል። እነዚህን ሰነዶች በኢንተርኔት፣ በስልክ ወይም በአካል ተገኝተው ማግኘት ይችላሉ። ሰነዶችን ከሚከተሉት ድረገጾች ዳውንሎድና ፕሪንት ማድረግ ይችላሉ www.uwmedicine.org/financialassistanceወይምwww.valleymed.org/financialassistance. ከዚህ በታች ለተጠቀሰው ቦታ፣ እንክብካቤ እየጠየቁ ወዳሉበት ቦታ፣ ደውለው ግልባጭ መጠየቅ ይችላሉ። ግልባጮች፣ በ UW Medicine የሐኪም ቤት ቦታዎች ውስጥ ባሉ የታካሚ መቀበያዎች እና የድንገተኛ ሕክምና ክፍል (Admissions and Emergency Departments) ውስጥ ይገኛሉ።

Airlift Northwest (Airlift)

Patient Financial Services
6505 Perimeter Road S., Ste 200
Seattle, WA 98108
206.965.1908 ፋክስ 206.521.1612
ሰኞ-ዓርብ 8:00 ጠዋት – 5:00 ከሰዓት

Harborview Medical Center (HMC)

Financial Counseling
325 9th Ave; Mail Stop 359758
Seattle, WA 98104-2499
206.744.3084
ሰኞ-ዓርብ 8:00 ጠዋት – 4:30 ከሰዓት

UW Medical Center (UWMC)

Financial Counseling
1959 NE Pacific Street, Mail Stop 356142
Seattle, WA 98195-6142​
206.598.3806
ሰኞ-ዓርብ 8:00 ጠዋት – 4:30 ከሰዓት

HMC & UWMC

Patient Financial Services
P.O. Box 95459
Seattle, WA 98145-2459
206.598.1950 ወይም 1.877.780.1121
ፋክስ 206.598.2360
ሰኞ-ዓርብ 8:00 ጠዋት – 4:30 ከሰዓት

Northwest Hospital & Medical Center (NWH)

Patient Financial Services
10330 Meridian Ave N Ste 260
Seattle, WA 98133-9851
206.668.6440 ወይም 1.877.364.6440
ሰኞ-ዓርብ 8:00 ጠዋት – 4:30 ከሰዓት

NWH Physicians

Patient Accounts & Inquiry
P.O. Box 45850
Seattle, WA 98145-0850
206.520.9100 ወይም 1.855.520.9100
ሰኞ-ዓርብ 9:00 ጠዋት – 5:00 ከሰዓት

UW Physicians (UWP) & UW Neighborhood Clinics (UWNC)

Patient Accounts & Inquiry
P.O. Box 50095
Seattle, WA 98145-5095
206.520.9300 ወይም 1.855.520.9300
ሰኞ-ዓርብ 9:00 ጠዋት – 5:00 ከሰዓት

Valley Medical Center (VMC)

Patient Financial Services
P.O. Box 59148
Renton, WA 98058-9900
425.251.5178 ፋክስ 206.575.2573
M-F ሰኞ-ዓርብ 8:00 ጠዋት – 5:00 ከሰዓት

የእንግሊዝና ቋንቋ ተናጋሪ ያልሆኑ

የፋይናንስ እርዳታ ፖሊሲ፣ የፋይናንስ እርዳታ ማመልከቻ፣ በግልጽ ቋንቋ የተጻፈ አጭር ዝርዝር፣ እና የቢል አደራረግ እና ዕዳ ስብሰባ ፖሊሲዎች ትርጉሞች በሚከተለው ድረገጽ ይገኛሉ www.uwmedicine.org/financialassistance ወይም www.valleymed.org/financialassistance፣ በአካል ተገኝተው ወይም እንክብካቤውን ወደሚጠይቁበት ቦታ ደውለው ማግኘት ይችላሉ።