የአስተዳደር ፖሊሲዎችና የአሰራር ደንቦች


የአስተዳደር ፖሊሲዎችና የአሰራር ደንቦች (PDF)​

ፖሊሲ

ይህ የፋይናንስ እርዳታ ፖሊሲ የታቀደው፣ በፌደራል የድህነት መመዘኛ ደረጃ ላይ ወይም በእዚያ አካባቢ ላይ ያሉ የዋሽንግተን ስቴት ነዋሪዎች፣ ተገቢ የሐኪም ቤት-ውስጥ-የሆኑ የሕክምና አገልግሎቶችን እና ተገቢ የሐኪም ቤት-ውስጥ-ያልሆኑ የሕክምና አገልግሎቶችን፣ ለአገልግሎቶቹ ለመክፈል ባላቸው አቅም መሠረት እስከሚሆኑ ወጪዎች ድረስና ያለምንም ወጪንም ጨምሮ እንዲያገኙ ተብሎ ነው። የፋይናንስ እርዳታ ለሁሉም ብቁ ለሚሆኑ ሰዎች፣ ዕድሜ፣ ዘር፣ የቆዳ ቀለም፣ ሀይማኖት፣ ጾታ፣ ጾታዊ ዝንባሌ ወይም የትውልድ ሐገርን በግምት ውስጥ ሳያስገባ በ WAC ምዕራፍ 246-453 እና RCW 70.170 መሰረት ይፈቀዳል።

የፖሊሲው መረጃ መገኘት

UW Medicine፣ ስለ የፋይናንስ እርዳታ ፕሮግራሙ ማስታወቅያ እንዲሰጥ ይጠበቅበታል እናም ስለ ፕሮግራሙ መኖር ለእያንዳንዱ ታካሚ መረጃ ለመስጠት በቀና መንፈስ የተቻለውን ያህል ጥረት ያደርጋል። የ UW Medicine ሐኪም ቤቶች (በሐኪም ቤት ለሚተኙና በሐኪም ቤት ውስጥ-የሆኑ የተመላላሽ ታካሚ ክሊኒኮች/ተቋሞች)፣ ስለ የፋይናንስ እርዳታ ፖሊሲ ለህዝብ የሚገልጽ ማስታወቅያ በ Admitting፣ Financial Counseling፣ Emergency Department እና Outpatient Registration ክፍሎች ውስጥ ምልክቶችን ይለጥፋሉ። የ POS 11 ይዘቶች እንደዚህ ዓይነቱ ማስታወቅያ እንዲለጠፍ የግድ አይጠይቁም። ለፋይናንስ እርዳታ ብቁ ለመሆን፣ ታካሚዎች በፋይናንስ እርዳታ ፖሊሲ ላይ የተገለጹትን ቅድመ ሁኔታዎችንና መስፈርቶችን ማሟላት ይኖርባቸዋል። ይህ የፋይናንስ እርዳታ ፖሊሲና ማመልከቻ፣ በሚመለከተው የሐኪም ቤት የአገልግሎት አካባቢ ውስጥ በሚገኝ ከአምስት በመቶ ሕዝብ ወይም ከ 1000 ያነሱ ግለሰቦች በሚናገሩት ማንኛውም ቋንቋ ተዘጋጅው ቀርበዋል። በተጨማሪም፣ የእንሊዝኛ ቋንቋ ለማይናገሩ ወይም የእንግሊዝኛ ቋንቋ ችሎታቸው የተወሰነ ለሆኑ ሰዎች፣ ወይም ሌሎች የጽሑፍ ማመልከቻን ማንበብ ወይም መረዳት ለማይችሉ ሰዎች፣ የቃል አስተርጓሚ አገልግሎት ይዘጋጅላቸዋል።

የቃላት ትርጉሞች

የፋይናንስ እርዳታ፥ UW Medicine፣ ስለ የፋይናንስ እርዳታ ፕሮግራሙ ማስታወቅያ እንዲሰጥ ይጠበቅበታል እናም ስለ ፕሮግራሙ መኖር ለእያንዳንዱ ታካሚ መረጃ ለመስጠት በቀና መንፈስ የተቻለውን ያህል ጥረት ያደርጋል። የ UW Medicine ሐኪም ቤቶች (በሐኪም ቤት ለሚተኙና በሐኪም ቤት ውስጥ-የሆኑ የተመላላሽ ታካሚ ክሊኒኮች/ተቋሞች)፣ ስለ የፋይናንስ እርዳታ ፖሊሲ ለህዝብ የሚገልጽ ማስታወቅያ በ Admitting፣ Financial Counseling፣ Emergency Department እና Outpatient Registration ክፍሎች ውስጥ ምልክቶችን ይለጥፋሉ። የ POS 11 ይዘቶች እንደዚህ ዓይነቱ ማስታወቅያ እንዲለጠፍ የግድ አይጠይቁም። ለፋይናንስ እርዳታ ብቁ ለመሆን፣ ታካሚዎች በፋይናንስ እርዳታ ፖሊሲ ላይ የተገለጹትን ቅድመ ሁኔታዎችንና መስፈርቶችን ማሟላት ይኖርባቸዋል። ይህ የፋይናንስ እርዳታ ፖሊሲና ማመልከቻ፣ በሚመለከተው የሐኪም ቤት የአገልግሎት አካባቢ ውስጥ በሚገኝ ከአምስት በመቶ ሕዝብ ወይም ከ 1000 ያነሱ ግለሰቦች በሚናገሩት ማንኛውም ቋንቋ ተዘጋጅው ቀርበዋል። በተጨማሪም፣ የእንሊዝኛ ቋንቋ ለማይናገሩ ወይም የእንግሊዝኛ ቋንቋ ችሎታቸው የተወሰነ ለሆኑ ሰዎች፣ ወይም ሌሎች የጽሑፍ ማመልከቻን ማንበብ ወይም መረዳት ለማይችሉ ሰዎች፣ የቃል አስተርጓሚ አገልግሎት ይዘጋጅላቸዋል።

በቤተሰብ ቁጥር መሠረት ተስተካክሎ ወይም ላገኙት እንክብካቤ ለመክፈል ወይም ለዲዳተክተብል (መቀነሻ ክፍያ) ወይም ለኮኢንሹራንስ (መቀናጆ ኢንሹራንስ) መጠን በሶስተኛ ከፋይ አካል እንደሚጠበቅባቸው ለመክፈል ገቢያቸው የማይበቃቸው ሰዎች፣ በዚህ ፖሊሲ ስር የፋይናንስ እርዳታ ብቁ ሊሆኑ ይችላሉ1

UW Medicine፥ ለዚህ ፖሊሲ ተግባር፣ “UW Medicine” ሲባል የሚያጠቃልለው፣ Airlift Northwest (Airlift)፣ Harborview Medical Center (HMC)፣ UW Medical Center (UWMC)፣ Northwest Hospital & Medical Center (NWH), UW Physicians (UWP)፣ Valley Medical Center (VMC)፣ እና UW Neighborhood Clinics (UWNC)ን ይሆናል።

ተገቢ የሐኪም ቤት-ውስጥ-የሆኑ የሕክምና አገልግሎቶች፥ እነዚያ የ UW Medicine ሐኪም ቤት አገልግሎቶች፣ ለሕይወት አስጊ፣ ወይም ለስቃይ ወይም ሕመም ምክንያት የሚሆኑ፣ ወይም ሕመምን ወይም የአካል አለመጠንከርን የሚያስከትሉ፣ ወይም ለአካል መታጎል ሁኔታ የሚያሰጉ ወይም ምክንያት የሚሆኑ፣ ወይም የሚያባብሱ፣ ወይም ለአካል ቅርጽ መቀየር ወይም መሰናከል ምክንያት የሚሆኑ እየተባባሱ የሚመጡ የሕመም ሁኔታዎችን መርምሮ ለማወቅ፣ ለማስተካከል፣ ለማዳን፣ ለማስታገስ ወይም ለመከላከል፣ እና አገልግሎቱን ለጠየቁት ታካሚ ሌላ በእኩል ደረጃ ፍቱን የሆነ፣ በይበልጥ የቁጠባ የሆነ፣ ወይም በጣም የአነስተኛ ወጪ ሕክምና  ለታካሚው የሚሆን የለም ወይም አመቺ ሕክምና እንዲሆኑ በተገቢው መንገድ የታሰቡ ናቸው። አንድ የሕክምና መንገድ ለሕመሙ ክትትል ማድረግን ብቻ ወይም ተገቢ ሲሆን ምንም ሕክምና አለማድረግንም ሊጨምር ይችላል። ተገቢ የሐኪም ቤት-ውስጥ-የሆኑ የሕክምና አገልግሎቶች፣ ከ UW Medicine ሐኪም ቤት ጋር ግንኙነት ቢኖራቸውም እንኳን፣ በአገልግሎት ቦታ 11 (POS 11) እራሳቸውን ችለው በሚንቀሳቀሱ ክሊኒኮች/የሐኪም ቢሮዎች ውስጥ የሚሰጠውን እንክብካቤ አይጨምርም። ቢሆንም፣ ቃሉ፣ በሐኪም ቤት ውስጥ በ HMC፣ UWMC፣ UWP፣ VMC፣ እና በ NWH ሰራተኞች እና የ NWH ሙሉ ንብረቶች በሆኑት የሕክምና መስጪያ ቅርንጫፍ ድርጅቶች የሚሰጡ የባለሙያ አገልግሎቶችን አይጨምር።

ተገቢ የሐኪም ቤት-ውስጥ፟-ያልሆኑ የሕክምና አገልግሎቶች፥ እነዚያ (1) በ Airlift፣ ወይም (2) በአገልግሎት ቦታ 11 (POS 11) እራሳቸውን ችለው በሚንቀሳቀሱ ክሊኒኮች/ በ UWP አባሎች የሐኪም ቢሮዎች ውስጥ፣ በ NWH ሰራተኞች፣ ወይም በ NWH ሙሉ ንብረቶች በሆኑት የሕክምና መስጪያ ቅርንጫፍ ድርጅቶች ሰራተኞች የሚሰጡ፣ ለሕይወት አስጊ፣ ወይም ለስቃይ ወይም ሕመም ምክንያት የሚሆኑ፣ ወይም ሕመምን ወይም የአካል አለመጠንከርን የሚያስከትሉ፣ ወይም ለአካል መታጎል ሁኔታ የሚያሰጉ ወይም ምክንያት የሚሆኑ፣ ወይም የሚያባብሱ፣ ወይም ለአካል ቅርጽ መቀየር ወይም መሰናከል ምክንያት የሚሆኑ እየተባባሱ የሚመጡ የሕመም ሁኔታዎችን መርምሮ ለማወቅ፣ ለማስተካከል፣ ለማዳን፣ ለማስታገስ ወይም ለመከላከል፣ እና አገልግሎቱን ለጠየቁት ታካሚ ሌላ በእኩል ደረጃ ፍቱን የሆነ፣ በይበልጥ የቁጠባ የሆነ፣ ወይም በጣም የአነስተኛ ወጪ ሕክምና የለም ወይም አመቺ ሕክምና እንዲሆኑ በተገቢው መንገድ የታሰቡ ናቸው። አንድ የሕክምና መንገድ ለሕመሙ ክትትል ማድረግን ብቻ ወይም ተገቢ ሲሆን ምንም ሕክምና አለማድረግንም ሊጨምር ይችላል። ለዚህ የፋይናንስ እርዳታ ፖሊሲ ተግባር ሲባል፣ የመከላከያ እንክብካቤ አገልግሎቶች እንደ “ተገቢ የሐኪም ቤት-ውስጥ፟-ያልሆኑ የሕክምና አገልግሎቶች” ተብለው ሊቆጠሩ ይችላሉ።

ድንገተኛ የሕክምና ሁኔታ፥ ጽኑ ህመምን ጨምሮ፣ ጠና ያሉ የሕክምና ምልክቶችን የሚያሳይ ሆኖ፣ ወዲያዉኑ የሕክምና እንክብካቤ ካልተገኘ የሚከተሉትን ያስከትላል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፥

 1. የግለሰቡን ጤና (ወይም እርጉዝ ሴት ከሆነች፣ የሴትዮዋን ወይም ያልተወለደውን ልጅ) ጽኑ አደጋ ላይ የሚጥል፤
 2. የአካል የእንቅስቃሴ ድርጊቶች በጽኑ መታጎል፤
 3. ማንኛውም የሰውነት ብልቶች ወይም ክፍል ላይ የከፋ ብልሽት የሚያደርስ።

ምጥ ለያዛት እርጉዝ ሴት ይህ ቃል የሚኖረው ትርጉም፥

 1. ህጻኑ ከመወለዱ በፊት ወደ ሌላ ሐኪም ቤት ለማዘወር በቂ ግዜ ሳይኖር፤ ወይም
 2. የሚደረገው ዝውውር፣ የሴትዮዋን ወይም ያልተወለደውን ልጅ ጤና ወይም ደህንነት አደጋ ላይ ሊጥል ከቻለ።

የአገልግሎት ቦታ 11 (POS 11)፥ ለዚህ ፖሊሲ ተግባር ሲባል፣ ይህ ቃል የሚያመለክተው፣ ሁሉንም የ UW Neighborhood ክሊኒኮች ጣቢያዎችን፣ እና ሌሎች እራሳቸውን ችለው የሚንቀሳቀሱ ክሊኒኮችን ወይም የጤና እንክብካቤ ባለሞያዎች አገልግሎቶችን ሰጥተው ለሙያቸው ክፍያ የሚያስከፍሉባቸው የሆስፒታሉ የሐኪም ቢሮዎች ያልሆኑትን ነው።

UW Physicians (UWP) አባላት፥ ለዚህ ፖሊሲ ተግባር ሲባል፣ አንድ ሐኪም ወይም ሌላ ከ UWP ጋራ ለሕክምና ተግባር ውልን የተፈራረመ ብቁ የሆነ የጤና እንክብካቤ ባለ ሞያ፣ ወይም ከ UWP ጋራ ባለው የኮንትራት ውል መሰረት ለሌላ አገልግሎቶቹን ያስተላለፈ፣ እና በተፈቀዱ የ UW Medicine ጣቢያዎች ውስጥ አገልግሎቶችን የሚሰጥን ያመለክታል።

የ NWH ሙሉ ንብረቶች የሆኑ የሕክምና መስጪያ ቅርንጫፍ ድርጅቶች፥ ለዚህ ፖሊሲ ተግባር ሲባል፣ ቃሉ የሚያጠቃልለው፣ Summit Cardiology ን እና በ NWH ሙሉ ባለቤትነት ስር የሆኑ ወይም ሊሆኑ የሚችሉ ማናቸውንም ሌሎች ቅርንጫፍ ድርጅቶችን እና ለፌደራል የታክስ ተግባር ሲባል እንደ ቅርንጫፍ ድርጅቶች የሚይቆጠሩትን ነው።

የብቁነት መስፈርቶች

የፋይናንስ እርዳታ የሚጠይቁ ሰዎች የብቁነት መስፈርቶችን ማሟላትና የማመልከቻ ሂደትን፣ እዚህ ላይ በተገለጸው መሰረት ማሟላት አለባቸው።

ነዋሪነትና የሚሰጡት የአገልግሎት ዓይነቶች

የፋይናንስ እርዳታ ብቁነት እንደሚጠይቀው፣ አንድ ሰው የዋሽንግተን ስቴት ነዋሪ መሆንና የሚጠየቁት የሕክምና አገልግሎቶች ተገቢ በሐኪም ቤት ውስጥ፟-የሆኑ የሕክምና አገልግሎቶች መሆን ይኖርባቸዋል፣ የምርመራ፣ ያማራጭ ወይም የጥናታዊ ሕክምናዎች ከመሆን ይልቅ። አንድ ነዋሪ የዋሽንግተን ስቴት ነዋሪ የማይሆነውና ለፋይናንስ እርዳታ ብቁ የማይሆነው የሕክምና እንክብካቤ ለማግኘት ጉዳይ ብቻ ወደ ዋሽንግተን ስቴት ከገባ ነው። ስደተኞች፣ የፖለቲካ ጥገኞች፣ እና የፖለቲካ ጥገኝነት እየጠየቁ ያሉት ሰዎች ለፋይናንስ እርዳታ ብቁነት ከዋሽንግተን ስቴት የነዋሪነት መስፈርት ነጻ ናቸው። እንዲሁም ደግሞ ከዋሽንግተን ስቴት የነዋሪነት መስፈርት ነጻ የሚሆኑት ድንገተኛ የሕክምና ሁኔታ ያለባቸው ሰዎች ናቸው። የፋይናንስ እርዳታ በኢሚግሬሽን ሁኔታ ምክንያት አይከለከልም። እነዚህ በዚህ አንቀጽ ላይ የተገለጹት የነዋሪነትና የአገልግሎት ዓይነት ልዩ አስተያየቶች፣ ሊደረጉ የሚችሉት በጣም ልዩ ሁኔታዎች ሲያጋጥሙና በ UW Medicine Chief Financial Officer ወይም በተሰያሚው ፈቃድ ከተሰጠ ብቻ ነው። የፌደራል ወይም የስቴት ሕጎች የሚጠይቁት ነገር ባይሆንም፣ የፋይናንስ እርዳታ ብቁነት ተገቢ የሐኪም ቤት-ውስጥ-ያልሆኑ የሕክምና አገልግሎቶች ለሚያገኙና ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች ለሚያሟሉ ግለሰቦችም የሚሰጥ ይሆናል።

ከሶስተኛ አካል የሚገኝ ሽፋን

የገንዘብ ድጋፍ ለሦስተኛ አካል ሽፋን በሁለተኛ ደረጃ ላይ ለሚገኙት ሁሉ ሌሎች ምንጮች ለታማሚው ይሰጣል። ይህም የሚከተሉትን ያጠቃልላል፥

 1. የቡድን ወይም የግል የሕክምና እቅዶች።
 2. የሰራተኛ ካሳ ፕሮግራሞች።
 3. Medicare፣ Medicaid ወይም ሌሎች የሕክምና እርዳታ ፕሮግራሞች።
 4. ሌሎች የስቴት፣ ፌደራል ወይም የውትድርና ፕሮግራሞች።
 5. የሶስተኛ-ወገን ተጠያቂነት (ላያቢሊቲ) ሁኔታዎች። (ለምሳሌ፥ የመኪና አደጋ ወይም የአካላዊ ጉዳቶች)።
 6. የትራይብ የጤና ጥቅማጥቅም
 7. ኸልዝ ኬር ሼሪንግ ሚኒስትሪ በ26 U.S.C Sec. 5000A. እንደተገለጸው
 8. ሌላ ሰው ወይም አካል ለሕክምና አገልግሎቶች የመክፈል ሕጋዊ ኃላፊነት ያለበት ሌሎች ሁኔታዎች።

ለነሱ የቀረቡ የመድን ዋስትና ሽፋንን (ለምሳሌ፣ Medicaid) የማግኛ ሂደትን ያልፈጸሙ፣ ነገር ግን ለፋይናንስ እርዳታ ብቁ የሚሆኑ ታካሚዎች፣ በግለሰብ ደረጃ ግምገማ ይደረግላቸዋል።

ለፋይናንስ እርዳታ ግምት ውስጥ ከመግባቱ በፊት፣ ታካሚው/ዋሱ ከሶስተኛ ወገን የክፍያ ሽፋን ማግኘት ይችል እንደሆነ ይገመገምና፣ ብቁ በሚሆንባቸው ፕሮግራሞች ውስጥ ታካሚው/ዋሱ ሽፋን ለማግኘት ማመልከቻ እንዲያስገባ ሊጠየቅ ይችላል። የፋይናንስ እርዳታ ማመልከቻ ቅድመ ሁኔታዎችን ማሟላት ያልቻለ ታካሚ፣ የፋይናንስ እርዳታ ከማግኘት ሊከለከል ይችላል። ለ Medicaid ብቁ እየሆኑ የ Medicaid ጥቅሞችን ለማግኘት የማያመለክቱ ታካሚዎች የፋይናንስ እርዳታ ሊከለከሉ ይችላሉ፤ ቢሆንም፣ UW Medicine፣ ታካሚው በ Health Benefits Exchange ላይ ለእርሱ በቀረበለት እቅድ ውስጥ ባለመመዝገቡ ምክንያት ብቻ ለታካሚ የፋይናንስ እርዳታ አይከለክልም።

ገቢ

በፖሊሲ መሰረት፣ ከፌደራል የድህነት መመዘኛ ደረጃ 300 በመቶ ወይም ከዚያ በታች ገቢ ያላቸው ሰዎች የፋይናንስ እርዳታ ለማግኘት ብቁ ሊሆኑ ይችላሉ። UW Medicine፣ አንድ ሰው ለፋይናንስ እርዳታ ብቁ መሆኑን ሲወስን ሁሉንም የገቢ ምንጮች ግምት ውስጥ ያስገባል። ገቢ ሲባል የሚያጠቃልለው፥ ከክፍያ ወይም ደሞዝ ታክስ ከመቆረጡ በፊት የተገኘ ጠቅላላ የጥሬ ገንዘብ መጠን፤ የዌልፌር ክፍያዎች፤ የሶሻል ሴኩሪቲ ክፍያዎች፤ የስራ ማቆም አድማኛ መደጎሚያ፤ የስራ አጥነት ወይም የአካል ስንክልና ጥቅሞች፤ የልጅ ማሳደጊያ አበል (ቻይልድሳፖርት)፣ የትዳር ባለቤት አበል (አሊሞኒ)፤ እንዲሁም ለታካሚው/ዋሱ፣ ከንግድ ድረጅቶችና የመዋለ ነዋይ ተግባሮች የተከፈለ የተጣራ ገቢ።

ማመልከቻ

አንድ ታካሚ የፋይናንስ እርዳታ ለመጠየቅ ማመልከቻ ማስገባት ሲፈልግ፣ ታካሚው በሚስጥር ተቀማጭ የፋይናንስ መረጃ (Confidential Financial Information (CFI)) ቅጽን መሙላትና በ CFI ውስጥ የተጻፉትን መረጃዎች የሚደግፉ አስፈላጊና ተገቢ የሆኑ የፋይናንስ ሰነዶችን ማቅረብ ይኖርበታል። UW Medicine፣ የአንድ ታካሚን የፋይናንስ እርዳታ ሁኔታ የመጀመሪያ ውሳኔ የሚያደርገው በምዝገባው ወቅት ወይም ለታካሚው አገልግሎቶቹ ከተጀመሩ በኋላ በተቻለ መጠን ወዲያዉኑ ይሆናል። የፋይናንስ እርዳታ ማመልከቻ ሂደቶች፣ ታካሚው የማመልከቻ ሂደቶቹ የሚጠይቁትን መስፈርቶች ከሟሟላት ሊከለክሉት የሚችሉ እንቅፋቶችን በግምት ውስጥ በማስገባት፣ ታካሚው ላይ ተገቢ ያልሆነ ጫና መፍጠር የለባቸውም። ለ Medicaid ወይም ለሌሎች ለሚመለከታቸው የመንግስት እርዳታ ጥቅሞች ብቁነት የሚደረግ ማጣሪያ በታካሚ መቀበያ ክፍል፣ የማሰናበቻ ዕቅድ/የውጤቶች አስተዳደር (Patient Access Department፣ Discharge Planning/Outcomes Management) (በነርሲንግ ሆም ምደባ ካልሆነ) በኩል ወይም በታካሚ ፋይናንስ አገልግሎቶች (Patient Financial Services) በኩል ይሆናል።

 1. ለፋይናንስ እርዳታ ብቁነት የመጨረሻ ውሳኔ መሠረት ለማድረግ ከሚከተሉት ሰነዶች ውስጥ ማንኛውም በቂ እንደሆነ ይቆጠራል፥
  1. የ “W-2” መያዣ ስቴትመንት፤
  2. ወቅታዊ የደሞዝ ቼክ ቀሪ ቁራጮች (የ 3 ወራት)፤
  3. የባንክ ስቴትመንት (የ 3 ወራት)፤
  4. ያለፈው ዓመት የታክስ ክፍያ ሰነድ፣ ቅጾችን (ስኬጁሎችን) ጨምሮ፣ የሚመለከትዎ ከሆነ፤
  5. የገቢ ማስረጃ ከሌለዎት፣ ከአሰሪዎችዎ ወይም ከሌሎች በጽሑፍ ተዘጋጅቶ የተፈረመበት ወቅታዊ የፋይናንስ ሁኔታዎን መግለጫ (የድጋፍ ደብዳቤ)፤
  6. ለ Medicaid እና/ወይም በስቴት ክፍያ ለሚደረግላቸው እርዳታዎች ፈቃድ መሰጠትዎን ወይም መከልከልዎን የሚያሳዩ ቅጾች፤
  7. የስራ አጥነት መደጎሚያ ብቁ እንዲሆኑ የፈቀዱልዎ ወይም ውድቅ የሚያደርጉ ቅጾች፤ ወይም ከአሰሪዎች ወይም ከዌልፌር ኤጀንሲዎች በጽሑፍ የተዘጋጁ ደብዳቤዎች።
 2. ከዚህ በተጨማሪ፣ ታካሚው ከዚህ በላይ ከተገለጹት ሰነዶች ውስጥ ምንም ማቅረብ በማይችልበት ወቅት፣ UW Medicine በኃላፊነት ከሚጠየቀው ወገን ወይም የአመልካቹን ገቢ ከሚገልጸው ሌላ ወገን ተጽፈው በተፈረመባቸው መግለጫዎች መሠረት ይተማመናል። ከላይ ከተጠቀሱት ውስጥ ምንም ሊገኝ ካልተቻለ፣ የ UW Medicine ከዚህ በፊት የተደረገ የፋይናንስ እርዳታ ስጦታን ወይም በተሰጠው የቃል መግለጫ ተሞርኩዞ UW Medicine ውሳኔ ሊያደርግ ይችላል።

UW Medicine፣ የፋይናንስ እርዳታ ብቁነት በግልጽ የሚታወቅ ከሆነ፣ የገቢ መስፈርቶችን፣ ሰነዶችንና የማረጋገጫ መስፈርትን ቀሪ ሊያደርግ ይችል ይሆናል። የማሕበራዊ ወይም የጤና ጉዳዮች ባሉባቸው ሁኔታዎች ላይ፣ የ UW Medicine ሰራተኞች የራሳቸውን አስተያየት በግምት ውስጥ ያስገባሉ። እንዲህ ባሉ ጉዳዮች ላይ፣ UW Medicine የመጨረሻ የብቁነት ውሳኔን ሲያደርግ፣ በኃላፊነት ከሚጠየቁት ወገኖች ተጽፈው በተፈረመባቸው መግለጫዎች ይተማመናል።

የፋናንስ መስፈርቶች

UW Medicine፣ የቤተሰቡ ጠቅላላ ገቢ ከወቅታዊው የፌደራል የድህነት መመዘኛ ደረጃ ከ 300 በመቶ እኩል ወይም በታች ለሆነ ማንኛውም ታካሚ/ዋስ፣ ለሙሉ የክፍያ ወጪ የፋይናንስ እርዳታ ይሰጣል።
በጣም ከባድ የፋይናንስ ችግር እንዳለባቸው የሚያሳዩ በሰነድ የተደገፉ ሁኔታዎች ካጋጠሙ፣ የቤተሰቡ ገቢ ከወቅታዊ የፌደራል የድህነት መመዘኛ ከ 300 በመቶ ለሚበልጥ ሰዎች፣ UW Medicine እንደ የፋይናንስ እርዳታ ቆጥሮ ያለባቸውን ዕዳ ሊሰርዝ ይችል ይሆናል። 2

በኃላፊነት የሚጠየቀው ወገን ከተገቢ የሐኪም ቤት ውስጥ፟-የሆኑ ወይም ተገቢ በሐኪም ቤት ውስጥ፟-ያልሆኑ የሕክምና አገልግሎቶች ጋራ ለሚገናኙ ወጪዎች ከፊሉን ወይም ሙሉ በሙሉ ከከፈለና፣ በኋላም በዚህ ፖሊሲ መሰረት የፋይናንስ እርዳታ መስፈርቶችን እንዳሟላ ከታወቀ፣ UW Medicine ታካሚው ለፋይናንስ እርዳታ ብቁ መሆኑን ካረጋገጠበት ቀን ጀምሮ በ 30 ቀኖች ውስጥ ኃላፊ ለሆነው አካል የከፈለው ገንዘቡ በሙሉ ተመላሽ ይሆናል። ተጨማሪ መረጃ በሚመለከታቸው ሐኪም ቤቶች የቢል አደራረግና ዕዳ ስብሰባ ፖሊሲ ውስጥ ሊገኝ ይችላል።

የአሰራር ደምብ

በኃላፊነት የሚጠየቁ ወገኖች፥ ለፋይናንስ ምክር መስጠት እና/ወይም የታካሚ ፋይናንስ አገልግሎቶች

A. መመሪያዎች/ቅድመ ተከተሎች

ወደ ዕዳ ሰብሳቢ ኤጀንሲ የተላለፉና በፍርድ ቤቱ ሥርዓት በኩል ፍርድ የተፈረደባቸው ሒሳቦች የበጎ አድራጎት እርዳታ ለማግኘት ብቁ መሆናቸው ይቀራል። አንድ ታካሚ፣ ለሒሳቡ የፍርድ ቤት ውሳኔ ከመግኘቱ በፊት በማንኛውም ግዜ ላይ ለበጎ አድራጎት እርዳታ ማመልከቻ ማስገባት ይችላል። ማመልከቻው የሚያካትተው፣ በሚስጥር ተቀማጭ የፋይናንስ መረጃ ቅጽን እና በሚስጥር ተቀማጭ የፋይናንስ መረጃ ቅጽ መመሪያዎችን (Confidential Financial Information Form and Confidential Financial Information Form Instructions) (የተያያዘውን ሰነድ 1ን ይመልከቱ) ሲሆን፣ እሱም ለፋይናንስ እርዳታ ግምገማ ሂደት የሚያስፈልጉ ሰነዶችን ዝርዝር ይገልጻል።

እንደ Medicaid እና Health Benefits Exchange ለመሳሰሉት ሌሎች ሽፋኖች ብቁነት ለታካሚዎች ማጣሪያ ይደረጋል።

ይህ ማመልከቻ፣ የድጋፍ ሰነዶች ካላቸው የፋይናንስ ሁኔታዎች መሉ መግለጫ ጋራ፣ ለብቁነት የመጨረሻ ውሳኔ ለማድረግ ገቢ ይሆናል።

UW Medicine፣ ለፋይናንስ እርዳታ ብቁነት ሁኔታ የመጀመሪያ ውሳኔ እስከሚደረግ ድረስ፣ የዕዳ ስብሰባ ጥረቶችን አይጀምርም። UW Medicine፣ ታካሚው ለፋይናንስ እርዳታ ብቁ ይሆናል ብሎ መጀመሪያ ውሳኔ በሚያደርግ ግዜ፣ ማንኛውምና ሁሉም የዕዳ ስብሰባ እርምጃዎች (የፍታብሔር ሕግ እርምጃዎች፣ ከደሞዝ ተቆራጭ ማስደረግ፣ እና ወደ ሰብሳቢ ወይም ክሬዲት ኤጀንሲዎች ማሳወቅንም ጨምሮ)፣ የመጨረሻ የፋይናንስ እርዳታ ብቁነት ውሳኔ እስከሚተላለፍ ድረስ እንዲቆሙ ይደረጋሉ። ቢሆንም፣ በ WAC 246-453-020 (5) ላይ በተደነገገው መሰረት፣ አንድ ታካሚ ወይም በኃላፊነት የሚጠየቀው ወገን በዚህ ፖሊሲ መሰረት የፋይናንስ እርዳታ የማመልከቻ ሂደትን በተገቢው መንገድ ማሟላት ካልቻለ፣ UW Medicine ታካሚውን የሚመለከት የዕዳ ስብሰባ ጥረቶችን ለመጀመር በቂ ምክንያት ይሆናል። በመሆኑም፣ ለዚህ ፖሊሲ ተግባር ሲባል፣ የፋይናንስ እርዳታ ማመልከቻ ሂደትን አንድ ታካሚ ወይም በኃላፊነት የሚጠየቅ ወገን በተገቢው መንገድ አላሟላም የሚባለው፣ ታካሚው ወይም በኃላፊነት የሚጠየቀው ወገን፣ የማመልከቻ ሰነዶቹን ካገኘበት ቀን ጀምሮ በ 15 የስራ ቀኖች ውስጥ የማመልከቻ ሰነዶቹን ሳያስገባ ሲቀር ነው። ታካሚው ወይም በኃላፊነት የሚጠየቀው ወገን ማመልከቻ በማስገባት ሂደቱ ላይ ዳግመኛ መሳተፍ ከጀመረ ማናቸውም የዕዳ ስብሰባ ጥረቶች እዲቆሙ ይደረጋሉ።

UW Medicine፣ የፋይናንስ እርዳታ ማመልከቻዎችና ደጋፊ ሰነዶችን ከተቀበለ በኋላ በ 14 ቀኖች ውስጥ የመጨረሻ ውሳኔውን ያደርጋል። ደጋፊ ሰነዶች ሲባሉ፣ በሚስጥር ተቀማጭ የፋይናንስ መረጃ ቅጽ መመሪያዎች (Confidential Financial Information Form Instructions) ላይ የተዘረዘሩትን ነገሮች ያጠቃልላሉ።

B. ማስታወቂያዎች

የ UW Medicine የፋይናንስ እርዳታ ለመጠየቅ ለሚያመለክቱ ሰዎች፣ የግለሰቡን የተሞላ የፋይናንስ እርዳታ ማመልከቻና ደጋፊ ሰነዶችን ካገኘ በኋላ የፋይናንስ እርዳታ ለማግኘት ብቁ ስለመሆናቸው ውሳኔውን በ 14 ቀኖች ውስጥ ያሳውቃቸዋል። የፋይናንስ እርዳታ ማመልከቻዎች ፈቃድ፣ ተጨማሪ መረጃ ጥያቄ፣ ወይም ውድቅ መሆን የሚገለጸው በጽሑፍ ሲሆን፣ የይግባኝ ወይም ጉዳዩ ዳግመኛ የሚታይበትን መመሪያዎች ይጨምራል። የ UW Medicine የፋይናንስ እርዳታ በሚከለክልበት ወቅት፣ የፋይናንስ እርዳታ ለጠየቀው ሰው ማመልከቻው ውቅድ የሆነው በምን መሰረት እንደሆነ UW Medicine ያሳውቀዋል። ከተከለከለ፣ ታካሚው/ዋሱ ለ UW Medicine ተጨማሪ ሰነዶችን ሊያቀርብ ወይም የተከለከለበት ማስታወቅያ በደረሰው በ 30 ቀኖች ውስጥ በዋና የፋይናንስ ሹም (Chief Financial Officer) ወይም በወኪላቸው ጉዳዩ እንዲገመገምለት ሊጠይቅ ይችላል። ግምገማው፣ ከዚህ በፊት የፋይናንስ እርዳታን ውድቅ ያደረገውን ውሳኔ ካጸደቀ፣ በስቴቱ ሕግ መሰረት ለታካሚው/ዋሱ እና ለጤና ጥበቃ ጽ/ቤት (Department of Health) በጽሑፍ ያስታውቃል።

C. ሰነዶችን በመዝገብ ማስቀመጥ

ከማመልከቻ ጋራ ዝምድና ያላቸው መረጃዎች ሁሉ በምስጢር ይቀመጣሉ። ማመልከቻውን የሚደግፉ የሰነዶች ግልባጮች ከፋይናንስ እርዳታ ማመልከቻ ቅጽ ጋራ አብሮ ይሆኑና ለሰባት ዓመት ይቀመጣሉ።

በዚህ ፖሊሲ ስር የተሸፈኑ የጤና እንክብካቤ ባለ ሞያዎች

እያንዳንዱ የ UW Medicine ሐኪም ቤት፣ በዚህ ፖሊሲ ስር ለአገልግሎቶቻቸው ሽፋን የሚደረግላቸውን የጤና እንክብካቤ ባለሞያዎች ስም ዝርዝር ይይዛል። እያንዳንዱን ሐኪም ቤት ያነጋግሩ ወይም ለእያንዳንዱ ሐኪም ቤት ስም ዝርዝሮች በ www.uwmedicine.org/financialassistance ድረገጽ ይመልከቱ፥

  • Harborview Medical Center
  • Northwest Hospital & Medical Center
  • UW Medical Center
  • Valley Medical Center

ማመሳከሪያ

 • Washington Administrative Code፣ ምዕራፍ 246-453፣ “የሐኪም ቤት የፋይናንስ እርዳታ” የሚከተሉትን በተለይ ሲጠቅስ፥
  • WAC 246-453-020 ድሃ ሰዎችን ለይቶ ማወቂያ ተመሳሳይ መመሪያዎች
  • WAC 246-453-030 ድሃ ሰዎችን ለይቶ ማወቂያ አሃዛዊ መረጃ መመዘኛ ነጥቦች
  • WAC 246-453-040 ድሃ ሰዎችን ለይቶ ማወቂያ ተመሳሳይ መስፈርቶች
 • RCW 70.170.060 የፋይናንስ እርዳታ — የተከለከሉና አስፈላጊ የሆኑ የሐኪም ቤቶች የአሰራር መንገዶችና ፖሊሲዎች
 • 26 USC §501(r)(5)(A) እና (B)
 • የ NWH የቢል አደራረግና ዕዳ ስብሰባ ፖሊሲ
 • የ VMC የቢል አደራረግና ዕዳ ስብሰባ ፖሊሲ
 • የ UWMC እና HMC የቢል አደራረግና ዕዳ ስብሰባ ፖሊሲ​
 • የ UW Medicine የፖሊሲ ቁጥር COM-007 – “የድንገተኛ ሕክምና እርዳታ እና ተፈጻሚ የሠራተኛ ሕግን (Emergency Medical Treatment and Active Labor Act (EMTALA)) ተግባራዊ ማድረግና መከተል”

አባሪ ሰነዶች፥

አባሪ ሰነድ 1፥ የፋይናንስ እርዳታ ማመልከቻና ቅጽ - በምስጢር የሚያዝ
የተገመገሙበት/የተከለሰበት ቀኖች፥ 3/2/2015፣ 3/23/2016፣ 4/18/2016፣ 10/2/2017, 10/1/2018


1 በዚህ ፖሊሲ ላይ ከተጻፉት የክፍያ መንገዶች ሌላ በተለየ ሁኔታ ክፍያዎች እንዲከፈሉ በሚጠይቁ በማናቸውም በፌደራል ገንዘብ በሚንቀሳቀሱ ፕሮግራሞች ውስጥ የመሳተፍ የ UW Medicine አካል የእያንዳንዱን ፕሮግራም የክፍያ መመዘኛ የሚከተል ይሆናል።

2 ይህም ከ Patient Protection እና Affordable Care Act ጋራ አብሮ የሚሄድ ሲሆን፣ ያለ-ትርፍ የሚሰሩ ሐኪም ቤቶች እና እንደ 501(c)(3) የሚታወቁ ድርጅቶች (Northwest Hospital እና Valley Medical Center ን ጨምሮ) ለድንገተኛ ሁኔታ ወይም በዚህ የፋይናንስ እርዳታ ስር እርዳታ ለማግኘት ብቁ ለሆኑ ግለሰቦች ሌላ አስፈላጊ የሕክምና እንክብካቤዎችን ሲሰጡ የሚያስከፍሉትን የገንዘብ መጠን መወሰን ይኖርባቸዋል። ለዚህ ዓይነት እንክብካቤ፣ የመድን ዋስትና ላላቸው ሰዎች ከሚያስከፍሉት በላይ ላለማስከፈልና እነዚህን ከመሰሉ ግለሰቦች “አጠቃላይ የክፍያ መጠን” ያለማስከፈል ፖሊሲ።  26 USC §501(r)(5)(A) እና (B) ይመልከቱ።   የ Northwest Hospital እና Valley Medical Center በዚህ ፖሊሲ መሰረት ለፋይናንስ እርዳታ ብቁ ለሆኑት ግለሰቦች ሁሉንም የክፍያ ሂሳቦች በመሰረዝ ይህን መመዘኛ ነጥብ ያሟላሉ። የ Northwest Hospital እና Valley Medical Center፣ የየራሳቸውን የዝቅተኛ ገቢ ነዋሪዎች የጤና እንክብካቤ ፍላጎቶችን ለሚያሟሉ ያለ-ትርፍ ለሚሰሩ የአካባቢና የመንግስት ኤጀንሲዎች ይህን ፖሊሲ አስመልክቶ መረጃ ይሰጣሉ።  በተጨማሪም፣ Northwest Hospital እና Valley Medical Center በግልጽ ቋንቋ የተጻፉ የዚህ ፖሊሲ አጭር ዝርዝሮችን፣ በሚመለከተው የሐኪም ቤት የአገልግሎት አካባቢ ውስጥ በሚገኝ ከ 5 በመቶ ሕዝብ ወይም ከ 1000 ያነሱ ግለሰቦች በላይ በሚናገሯቸው ቋንቋዎች ተዘጋጅተው ቀርበዋል።  Northwest Hospital እና Valley Medical Center፣ የዚህን ፖሊሲ ግልባጭ፣ በግልጽ ቋንቋ የተጻፈውን የፖሊሲ አጭር ዝርዝር፣ እና ማመልከቻ ያለ ምንም ክፍያ ከድረገጻችው፣ የሕክምና አገልግሎቶች ከሚፈጸሙባቸው ቦታዎች በጥያቄ እና በ US Mail ማግኘት ይቻላል፥  Northwest Hospital Patient Financial Services, 10330 Meridian Ave N., Suite 260, Seattle, WA 98133-9851፤ (206) 668-6440 ወይም (877) 364-6440፤ (የሚከፈተው ሰኞ እስከ ዓርብ፣ 8:00 ጠዋት እስከ 4:30 ከሰዓት) እና Valley Medical Center Financial Counseling, 400 South 43rd St., Renton, WA 98055-5010፤ (425) 251-5178፤ (የሚከፈተው ሰኞ እስከ ዓርብ፣ 8:30 ጠዋት እስከ 5:00 ከሰዓት)።