የፋይናንስ እርዳታ ማመልከቻ ቅጽ መመሪያዎች


Instructions

ይህ በ UW Medicine የፋይናንስ እርዳታ ማመልከቻ ነው (ደግሞ የበጎ አድራጎት እንክብካቤ ተብሎ ይታወቃል)። የዋሽንግተን ስቴት፣ ሁሉም ሐኪም ቤቶች የተወሰኑ የገቢ መስፈርቶችን ለሚያሟሉ ሰዎችና ቤተሰቦች የፋይናንስ እርዳታ እንዲያቀርቡ ያዛል። በቤተሰብዎ ብዛትና የገቢዎ መጠን መሰረት፣ የጤና የመድን ዋስትና ቢኖርዎ እንኳን፣ ለፋይናንስ እርዳታ ብቁ ሊሆኑ ይችላሉ። እርዳታ የሚሰጥዎት የፋይናንስ እርዳታ መመሪያዎችን ካሟሉ ነው፣ እሱም የቤተሰብዎ ገቢ ከፌደራል የድህነት መመዘኛ ደረጃ 300 በመቶ እኩል ወይም ከዚያ በታች መሆኑን ይጨምራል። ተጨማሪ መረጃ መጠየቅ ወይም በሚከተለው የፋይናንስ እርዳታ ድረገጻችን www.uwmedicine.org/financialassistance ወይም www.valleymed.org/financialassistance መመልከት ይችላሉ።

የፋይናንስ እርዳታ ማመልከቻን አውርድ (PDF)

የፋይናንስ እርዳታ የሚሸፍነው ምንድን ነው?

የሐኪም ቤት የፋይናንስ እርዳታ የሚሸፍነው በእርስዎ ብቁነት መሠረት በ UW Medicine ለሚሰጡ ተገቢ ለሆኑ የሐኪም ቤት-ውስጥ አገልግሎቶች ነው። የፋይናንስ እርዳታ፣ በሌላ ድርጅቶች የሚሰጡ አገልግሎቶችን ጨምሮ፣ ሁሉንም የጤና እንክብካቤ ወጪዎችን ላይሸፍን ይችላል።

ማመልከቻዎ ተፈጻሚ እንዲሆን ለማድረግ ያለብዎት ነገሮች፦

  • ስለ ቤተሰብዎ መረጃ ለእኛ መስጠት፤ በቤተሰብዎ ውስጥ ያለውን የአባላት ቁጥርን ይጻፉ (ቤተሰብ ሲባል የሚያጠቃልለው፣ አብረው የሚኖሩ የሥጋ ዘመድ፣ የጋብቻ ወይም ጉዲፈቻ ዘመድን ነው)
  • ስለ ቤተሰብዎ አጠቃላይ ወርሐዊ ገቢ (ታክስ ከመከፈሉና ተቀናሽ (ዲዳክሽ) ከመደረጉ በፊት ያለውን ገቢ) መረጃ ይስጡን
  • ስለ የቤተሰብዎ ገቢና ለሚያሳውቋቸው ንብረቶች ሰነዶችን ያቅርቡ
  • አስፈላጊ ከሆነ ተጨማሪ መረጃ አያይዘው ያቅርቡ፣ ለምሳሌ፣ ለመረጃዎ ድጋፍ የሚሆኑ ደብዳቤዎችን ያቅርቡ
  • ቅጹ ላይ ይፈርሙና ቀኑን ይጻፉ

ማሳሰቢያ፥ የፋይናንስ እርዳታ ማመልከቻ ለማስገባት የሶሻል ሴኩሪቲ ቁጥር መስጠት የግድ አስፈላጊ አይሆንም። የሶሻል ሴኩሪቲ ቁጥርዎን ከሰጡን የማመልከቻዎን ሂደት ለማፋጠን ይረዳናል። የሶሻል ሴኩሪቲ ቁጥሮች ለእኛ የሚሰጠንን መረጃ ለማረጋገጥ ይረዳናል። የሶሻል ሴኩሪቲ ቁጥር ከሌለዎት፣ “አይመለከተኝም” ወይም “NA” ብለው ምልክት ያድርጉበት።

የተሞላውን ማመልከቻዎን ከሁሉም ሰነዶች ጋራ ከዚህ በታች ምልክት ወደ ተደረገበት የ UW Medicine የአገልግሎት ክፍል ያቅርቡ። ለራስዎ አንድ ግልባጭ መያዝዎን ያረጋግጡ።

Airlift Northwest (Airlift)

Patient Financial Services
6505 Perimeter Road S., Ste 200
Seattle, WA 98108
206.965.1908 ፋክስ 206.521.1612
ሰኞ-ዓርብ 8:00 ጠዋት – 5:00 ከሰዓት

Harborview Medical Center (HMC)

Financial Counseling
325 9th Ave; Mail Stop 359758
Seattle, WA 98104-2499
206.744.3084
ሰኞ-ዓርብ 8:00 ጠዋት – 4:30 ከሰዓት

UW Medical Center (UWMC)

Financial Counseling
1959 NE Pacific Street, Mail Stop 356142
Seattle, WA 98195-6142​
206.598.3806
ሰኞ-ዓርብ 8:00 ጠዋት – 4:30 ከሰዓ.

HMC & UWMC

Patient Financial Services
P.O. Box 95459
Seattle, WA 98145-2459
206.598.1950 ወይም 1.877.780.1121
ፋክስ 206.598.2360
ሰኞ-ዓርብ 8:00 ጠዋት – 4:30 ከሰዓት

Northwest Hospital & Medical Center (NWH)

Patient Financial Services
10330 Meridian Ave N Ste 260
Seattle, WA 98133-9851
206.668.6440 ወይም 1.877.364.6440
ሰኞ-ዓርብ 8:00 ጠዋት – 4:30 ከሰዓት

NWH Physicians

Patient Accounts & Inquiry
P.O. Box 45850
Seattle, WA 98145-0850
206.520.9100 ወይም 1.855.520.9100
ሰኞ-ዓርብ 9:00 ጠዋት – 5:00 ከሰዓት

UW Physicians (UWP) & UW Neighborhood Clinics (UWNC)

Patient Accounts & Inquiry
P.O. Box 50095
Seattle, WA 98145-5095
206.520.9300 or 1.855.520.9300
ሰኞ-ዓርብ 9:00 ጠዋት – 5:00 ከሰዓት

Valley Medical Center (VMC)

Patient Financial Services
P.O. Box 59148
Renton, WA 98058-9900
425.251.5178 ፋክስ 206.575.2573
ሰኞ-ዓርብ 8:00 ጠዋት – 5:00 ከሰዓት

ጥያቄዎች ካልዎትና ይህን ማመልከቻ በመሙላት ላይ እርዳታ የሚያስፈልግዎ ከሆነ፣ ካላይ የተጠቀሰውን የአገልግሎት ተቋም ያነጋግሩ። ለአካል ስንክልና እና ለቋንቋ እርዳታን ጨምሮ፣ ለማንኛውም ምክንያት እርዳታ ማግኘት ይችሉ ይሆናል።

ለብቁነትዎና የይግባኝ መብቶችዎ፣ የሚመለከትዎ ከሆነ፣ ለምናደርገው የመጨረሻ ውሳኔ፣ የገቢዎን ማረጋገጫ ሰነዶችን ጨምሮ፣ የተሞላው የፋይናንስ እርዳታ ማመልከቻ ከደረሰን ቀን ጀምሮ በ 14 የካላንደር ቀኖች ውስጥ እናሳውቅዎታለን።

የፋይናንስ እርዳታ ማመልከቻ በማስገባትዎ፣ የፋይናንስ ግዴታዎችንና መረጃን ለማረጋገጥ የሚያስችሉንን አስፈላጊ ምርመራዎች እንድናደርግ ፈቅደውልናል ማለት ነው።

ለመርዳት እንፈልጋለን። እባክዎን ማመልከቻዎን ወዲያው ያስገቡ!
መረጃዎ እስከሚደርሰን ድረስ ቢሎች ሊደርስዎ ይችሉ ይሆናል።strong>

የፋይናንስ እርዳታ ማመልከቻን አውርድ (PDF​)