የክትባት እና የምርመራ መስፈርቶች

የሃርበርቪው ህክምና ማዕከል ሙሉ የኮቪድ-19 ክትባት አለያም ባለፉት 3 ቀናት ውስጥ የተደረገ የኮቪድ-19 ምርመራ ነፃ ማረጋገጫዎችን ይፈልጋል፡፡ይህ መስፈርት በዋሽንግተን ዩኒቨርስቲ ህክምና ማዕከል በሚገኙት የማውንትሌክ ቴሬስ ሆስፒታል እና የኖርዝዌስት ሆስፒታል ቅጥር ግቢዎች በዲሴምበር 6 2021 ይጀመራል፡፡  

ይህ ተፈላጊ መስፈርትም ፡-

 • ከ 12 ዓመት በላይ ለሆናቸው የአዳሪ ታካሚ ጎብኝዎች 
 • ከ 18 ዓመት በላይ ለሆናቸው እና ከአዋቂ/ጎልማሳ ታካሚዎች ጋር ወደ ክሊኒክ ለሚመጡ ሰዎች ነው የሚመለከተው፡፡

ታካሚዎች የክትባት ማረጋገጫ ወይም የምርመራ ነፃ ማረጋገጫ ማሳየት አይጠበቅባቸውም፡፡

ስለ የክትባት መስፈርት

"ሙሉ በሙሉ የተከተበ" የሚለውን መስፈርት ለማሟላት ፡- 

 • 2ኛ ዙር የፋይዘር አለያም የሞደርና ክትባትን ከተከተቡ ቢያንስ 2 ሳምንት ያደረጉ ወይም
 • 1ኛ ዙር የጆንስን እና ጆንሰን ክትባትን ከተከተቡ ቢያንስ 2 ሳምንት ያደረጉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡

የክትባት ማረጋገጫዎች የሚከተሉትን ያካትታል

Vaccine card

የክትባት ካርድ፡

Vaccine card on phone

የክትባት ካርድ ፎቶ (ፊትና ጀርባ )-

Website on phone

ከ ማይ ኣይ ኣር ሞባይል.ኮም https://myirmobile.com የተወሰደ- የዲጂታል መረጃ ወይም በኤሌክትሮኒክሰ መልክ የቀረበ የጤና መረጃ

Vaccine card on website

ከ ማይ ኣይ ኣር ሞባይል.ኮም https://myirmobile.com ወይም ጤና ክብካቤ አቅራቢ የቀረበ ማስረጃ ወረቀት

COVID test results

ስለ ምርመራው ተፈላጊ መስፈርት

ከ ፀረ-እንግዳ (አንቲ ቦዲ) የደም ምርመራ ውጤት በስተቀር ሁሉም የኮቪድ-19 ምርመራዎች ተቀባይነት አላቸው፡፡የነፃ (ኔጌቲቭ) ምርመራ ማረጋገጫው የወረቀት ወይም የኤሌክትሮኒክ መረጃ ሲሆን የሚከተሉትን የግድ ማካተት አለበት፡፡

 • የተመርማሪውን ሙሉ ስም
 • የተደረገው የምርመራ አይነት
 • የምርመራ ውጤት
 • ምርመራው የተከናወነበት ቀን (ምርመራው የግድ ከጉብኝት ዕለት 3 ቀናት አስቀድሞ የተደረገ መሆን ይኖርበታል)፡፡

ለኮቪድ-19 ክትባትዎ እንዴት ቀጠሮ መያዝ እንደሚችሉ

የክትባት ጣቢያዎች የዋሽንግተን ዩኒቨርስቲ በዋሽንግተን ዩኒቨርስቲ ህክምና ማዕከል-ኖርዝዌስት፣ በዋሽንግተን ዩኒቨርስቲ ህክምና ማዕከል -ማውንትሌክ፣በሃርበርቪው ህክምና ማዕከል እና ሾርላይን በሚገኘው የዋሽንግተን ዩኒቨርስቲ ህክምና የኖርዝ ኪንግ ካውንቲ ክትባት ክሊኒክ የክትባት ጣቢያዎች አሉት፡፡ ካለ ቀጠሮ ለመታየት ያሉትን አማራጮች ለመጠቀም እባክዎን www.uwmedicine.org/coronavirus/vaccine ን ይመልከቱ፤ ከመምጣትዎ በፊትም የስራ ሰዓታችንን ይወቁ፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የተመረጡ ስፔሻሊቲ ክሊኒኮችን እና የመጀመሪያ/ተቀዳሚ ክብካቤ ክሊኒኮችን ጨምሮ ከ 20 በላይ በሆኑ የተመላላሽ ታካሚዎች ክሊኒኮች የዋሽንግተን ዩኒቨርስቲ ህክምና ክትባቶችን ይሰጣል፡፡ ከነኝህ ክሊኒኮች በአንዱ ክትባት ለማግኘት የግድ ቀጠሮ ሊኖርዎት ይገባል፡፡

ለኮቪድ-19 ምርመራዎ እንዴት ቀጠሮ መያዝ እንደሚችሉ

ለዋሽንግተን ዩኒቨርስቲ ሆስፒታሎች ቅርብ የሆኑ የምርመራ ጣቢያዎች

የዋሽንግተን ዩኒቨርስቲ ህክምና በ 4 ሆስፒታሎቹ እና በአቅራቢያው የምርመራ ጣቢያዎች አሉት፡፡ በነዚህ ጣቢያዎች ለመመርመር የግድ ቀጠሮ መያዝ ይኖርበዎታል፡፡

 •  ዩ-ዲስትሪክት የምርመራ ጣቢያ ፡- ከማውንትሌክ- ዋሽንግተን ዩኒቨርስቲ ህክምና ማዕከል በእግር ጉዞ ሊኬድበት የሚችል
 • በዋሽንግተን ዩኒቨርስቲ ህክምና ማዕከል-ኖርዝዌስት 
 • አውሮራ የምርመራ ጣቢያ ፡- ለዋሽንግተን ዩኒቨርስቲ ህክምና ማዕከል-ኖርዝዌስት ቅርብ የሆነ
 •  ሃርበርቪው ህክምና ማዕከል
 • ቫሊ ህክምና ማዕከል

ሌሎች የምርመራ ጣቢያዎች

 • የዋሽንግተን ዩኒቨርስቲ ህክምና የላብራቶሪ ህክምና በሲያትል ዙሪያ የምርመራ ጣቢያ አለው፡፡ ለወቅታዊ የምርመራ ጣቢያዎች ዝርዝር እና ያለቀጠሮ ለመቅረብ ያሉ አማራጮች ይህን ይጎብኙ፡- www.uwmedicine.org/coronavirus/testing.
 • በደወሉበት ቀን እንደሚመረመሩ እነኝህ ጣቢያዎች ዋስትና ሊሰጡ አይችሉም፡፡
 • እነኝህ ጣቢያዎች ፈጣን /ራፒድ ምርመራ አይሰጡም፡፡ ዉጤትዎን ከማግኘትዎ በፊት 48 ሰዓታት መሙላት ይኖርበታል፡፡

የቤት ውስጥ ምርመራ

ከላይ የተገለፁት የምርመራ ጣቢያዎች ለቅርብ/ለአሁን የኮቨድ-19 ልክፍት (ኢንፌክሽን ) የወቅቱን እና ቀላል (ሴንሲቲቭ) ምርመረዎችን ይጠቀማሉ፤ ነገር ግን ከ ፀረ-እንግዳ (አንቲ ቦዲ) የደም ምርመራ ውጤት በስተቀር እኛ ሁሉንም የኮቪድ-19 ምርመራዎችን እንቀበላለን፡፡ ፈጣን /ራፒድ የቤት ውስጥ ምርመራ የት ማግኘት እንዳለብዎት እና ኢንሹራንስዎ እንዲሸፍንልዎት ምን ማድረግ እንዳለብዎት ለማወቅ ይህንን ይጎብኙ www.covidtests.gov