ኮቪድ-19 የሕሙማን ጠያቂዎች መመሪያ

የሕክምና ማዕከል እንክብካቤ ለማግኘት ምርጫዎት የዋሽንግተን ዩኒቨርስቲ ሒክምና ማዕከል (UW Medical Center) ስለሆነ እናመሰግናለን ፡፡ ስለታካሚዎቻችን ፣ ቤተሰቦቻቸው ፣ ተንከባካቢዎቻችን እና ማህበረሰባችን ጤንነት እና ደህንነት እናስባለን (ግድ ይለናል)።

እንደምታውቁት በአካባቢያችን ያሉ ሰዎች በኮሮና ረቂቅ ተህዋሲ (ኮቪድ-19)ተጠቂ ሆነው ተገኝተዋል። ይህ ረቂቅ ተህዋሲ ሊሰራጭ ስለሚችል የእያንዳንዱን ሰው ደህንነት ለመጠበቅ የተወሰኑ እርምጃዎችን እየወሰድን ነው ፡፡ እንደ ሁሌም  የሕመምተኞቻችን ጤንነት እና ደኅንነት ወነኛ ጉዳያችን ነው ፡፡

ከየካቲት 27 ቀን 2012 ዓ.ም.(March 6, 2020) ጀምሮ ወደ ሆስፒታሉ የሚመጡትን ጠያቂዎች ብዛት ገደብ ማድረግ እንጀምራለን፦

  • እርጉዝ ታካሚዎች አንድ አጋር እና አንድ የወሊድ ጊዜ ድጋፍ ሰጪ ሰው አብሯቸው ሊኖራቸው ይችላል ፡፡
    • ከ 16 ዓመት በታች ለሆኑ ልጆች አይፈቀድም
  • ለፅኑ ሕመምተኛ ሕፃናት ማቆያ ክፍል
    • ወላጅ እንዲሁም አንድ ሌላ አጋር ወዳጅ
    • በየቀኑ የሚመጡት እነዛው ግለሰቦች መሆን አለባቸው
  • የሕይወት መጨረሻ ደረጃ ላይ ላሉ ህመምተኞች 2 ብቻ  ጠያቂዎች ሊኖራቸው ይችላሉ ፡፡
    • ግለሰቦች እነዛ ሁለቱ መሆን አለባቸው
    • ለጥየቃ ሲመጡ ጨርሰው እስከሚወጡ ድረስ እዛው ክፍሉ ውስጥ መቆየት አለባቸው
  • በአሁኑ ጊዜ የባህሪ እንክብካቤ ዕቅድ ያላቸው ታካሚዎች የቤተሰብ አባል ለእነሱ እንክብካቤያቸው ቁልፍ ከሆነ 1 ጠያቂ ብቻ ሊኖር ይችላል
    • ያው ግለሰብ መሆን አለበት
    • ያው ግለሰብ መሆን አለበት
  • ወደ ቤት ለመሄድ ለመለቀቅ ደሕነትን ለማረጋገጥ የቤተሰብ አባል ስልጠና የሚሹ ታካሚዎች
    • ያው ግለሰብ መሆን አለበት
    • ያው ግለሰብ መሆን አለበት
  • ሁሉም ጠያዊዎች የሚመረመሩ እና ከሕመም ስሜት ነፃ መሆን አለባቸው
  • በአሁኑ ሰዓት ሌላ ጠያቂዎች ሕክምና ማዕከል ውስጥ እንዲገቡ አይፈቀድላቸውም
  • የድንገተኛ ጊዜ ሕክምና ካልሆነ  በስተቀር ሁሉም ሰው ወደ ሕክምና ማዕከሉ ለመግባት ዋናው በር መጠቀም አለበት

የዋሽንግተን ዩኒቨርስቲ ሒክምና ማዕከል (UW Medical Center) ላይ - የተመሰረተ የተመላላሽ ክሊኒክ ቀጠሮ ወይም የድንገተኛ ሕክምና ከሆነ የመጡት 1 ድጋፍ ሰጪ ሰው ከእርስዎ  ጋር ማምጣት ይችላሉ

የጠያቂዎች መገደብ አስፈላጊነት ምቹ አለመሆኑን እናውቃለን። በዚህ ጊዜ ላሳዩት ትዕግስት እና ግንዛቤ (መረዳት)እናመሰግናለን ። እኛ ቅድሚያችን እርስዎን  እና ቤተሰብዎን ለመከላከልና  እና በጣም የተሻለ እንክብካቤ መስጠት ነው።

በዚህ አዲስ መመሪያ (ፖሊሲ) ላይ የሚደረጉ ማንኛቸውም ለውጦች አድርገን እናሳውቅዎታለን።  ልክ ደህንነቱ እንደተጠበቀ ወደ ወትሮው (ተለመደው) የጠያቂ መመሪያዎች ወዲያውኑ እንመለሳለን